መልዕክት ለወጣቶች
ወጣቶች እንደ ነፍስ ማራኪዎች
ሰይጣን ወጣቶችን እግዚአብሔር ከሚቀበለው መንገድ ሙሉ በሙሉ ተቃራኒ በሆነ መንገድ ሊመራቸው ያቀደ ንቁ ጠላት ነው፡፡ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሊያደርጉት የሚችሉትን መልካም ሥራ ለመሥራት የሚችል ሌላ ህዝብ እንደሌለ በደንብ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ወጣቶች ትክክለኛ ከሆኑ ኃይለኛ ተጽእኖ ማሳደር ይችላሉ፡፡ ለእግዚአብሔር ሥራ ራሳቸውን የለዩ ወጣቶች በመሰሎቻቸው ላይ ሊያሳድሩት የሚችሉትን ተጽእኖ ግማሹን ያህል እንኳን ሰባኪያን ወይንም በእድሜ የገፉ ፈቃደኛ አገልጋዮች ሊያሳድሩ አይችሉም፡፡ ደስታቸውንም ሆነ የተፈጥሮ ፍላጎታቸውን በመሰዋት መሰል ሟች የሆኑ ሰዎችን ለማዳን ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ ኃላፊነቱ በእነርሱ ላይ እንደሚያርፍ ሊሰማችው ይገባል፡፡ ጊዜና አስፈላጊ ከሆነ ገንዘብም ለእግዚአብሔር መቀደስ አለበት፡፡ MYPAmh 135.1
እግዚአብሔርን እናመልካለን የሚሉ ሁሉ ከክርስቶስ ውጭ ያሉ ሰዎች ያለባቸው አደጋ ሊሰማቸው ይገባል፡፡ የምህረት ጊዜያቸው በቶሎ ይዘጋል፡፡ በእግዚአብሔር ምክር ቢቆሙ ኖሮ ነፍሳትን ለማዳን ታላቅ ታጽእኖ ማሳደር ይችሉ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ከራስ ወዳድነታቸውና ከስንፍናቸው ወይም በክርስቶስ መስቀል በማፈራቸው ምክንያት ተግባራቸውን ያልፈፀሙ ሰዎች የራሳቸውን ነፍስ ማጣት ብቻ ሳይሆን የምስኪን ኃጢአተኛ ነፍሳት ደም በልብሶቻቸው ለይ ይኖራል፡፡ እነዚህ ሰዎች ለእግዚአብሔር ተቀድሰው ቢሆን ኖሮ ሊሰሩት ስለሚችሉት ጥሩ ሥራ ግን ታማኝነት ስለሌላቸው ሳይፈጽሙት ስለ ቀሩት ይጠየቃሉ፡፡ MYPAmh 135.2
የሚያድን ፍቅርን ጣፋጭነት በርግጥ የቀመሱ ሰዎች ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ሁሉ ከደህንነት እቅድ ጋር እስኪተዋወቁ ድረስ አያርፉም፤ ሊያርፉም አይችሉም፡፡ ወጣቶች «ጌታ ምን እንዳደርግ ትፈልጋለህ? በምድር ላይ ስምህን እንዴት አድርጌ ላከፍርና ከፍ ከፍ ላደርግ እችላሉ?” ብለው መጠየቅ አለባቸው፡፡ ነፍሳት በዙሪያችን ሁሉ እየጠፉ ናቸው፤ ግን ነፍሳትን ለክርስቶስ ለመማረክ ወጣቶች ምን ሸክም ይሸከማሉ? MYPAmh 135.3