መልዕክት ለወጣቶች

220/511

ለሌሎች ደህንነት ማሰብ

ተማሪዎች ለአዳኙ ነፍሳትን ማዳን ይችሉ ነበር፤ ነገር ግን የክርስቶስን ስም የሚጠራ ማን ነው? ጓደኞቻቸውን ትህትና በተሞላ ትጋት የኃጢአትን መንገድ እንዲተውና የቅድስናን መንገድ እንዲመርጡ እየተማፀኑአቸው የሚታዩ እነማን ናቸው? MYPAmh 135.4

አማኝ ወጣቶች መከተል የሚገባቸው መንገድ ይህ ነው፤ ነገር ግን አያደርጉትም፡፡ ከኃጢአተኞች ጋር በስፖርትና ደስታን ፍለጋ አንድነት መፍጠር ለስሜቶቻቸው እጅግ ይመቻቸዋል፡፡ ወጣቶች ጠቃሚዎች መሆን የሚችሉበት ሰፊ ምህዳር አላቸው፣ ነገር ግን አያዩትም፡፡ አሁን ምነው እየጠፉ ላሉት ነፍሳት የቅድስናን መንገድ ለማሳወቅና በፀሎትና በልመና አንድ ነፍስን እንኳን ለማዳን የአእምሮ ኃይላቸውን በተጠቀሙ! MYPAmh 135.5

አንድ ሰው ለዘላለም እግዚአብሔርን ለማመስገን መብቃት እንዴት ያለ የከበረ ሥራ ነው! አንድ ነፍስ ደስታንና የዘላለም ህይወትን ማግኘት መቻል፣ አንድ እንቁ በዘውዳቸው ላይ እንደ ኮከብ ከዘላለም እስከ ዘላለም ማብራት መቻል እንዴት የከበራ ሥራ ነው! ነገር ግን ከአንድ ነፍስ በላይ ከስህተት ወደ እውነት፣ ከኃጢአት ወደ ቅድስና እንዲመለሱ ማድረግ ይቻላል፡፡ ጌታ በነብዩ አማካይነት እንዲህ ብሏል፡- «ብዙዎችን ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ያበራሉ፡፡» እየጠፉ ያሉትን ነፍሳት በማዳን ሥራ ላይ ከክርስቶስና ከመላእክቱ ጋር ተሰማርተው ያሉ በእግዚአብሔር መንግስት ብዙ ሽልማት ይጠብቃቸዋል፡፡ MYPAmh 135.6

ወጣቶች ራሳቸውን ለእግዚአብሔርና ለእውነት ቀድሰው መሆን በሚገባቸው ቦታ ቢሆኑ ኖሮ ብዙ ወጣቶች መዳን እንደሚችሉ አየሁ፡፡ ነገር ግን በአጠቃላይ ራሳቸውን ቋሚ ሥራ ሊሰጣቸው በሚችልበት ቦታ ያስቀምጣሉ፤ ያለበለዚያም ራሳቸው ከዓለም ይሆናሉ፡፡ የሁልጊዜ ስጋትና የልብ ጭንቀት ምንጭ ናቸው፡፡ ስለ እነርሱ እንባዎች ይፈርሳሉ፤ ስለ እነርሱ ከወላጆች ልብ የመቃተት ፀሎቶች ይወጣሉ፡፡ ሆኖም የሚከተሉት የተግባር አቅጣጫ ለሚያስከትለው ሥቃይ ግድ የለሽ በመሆን ወደ ፊት ይቀጥላሉ፡፡ እነርሱን ለማዳንና በክርስቶስ ኢየሱስ ደም አማካይነት እግዚአብሔር እንዳቀደላቸው ሆነው እንዲገኙ ለማድረግ ለመሞት ፈቃደኛ በሆኑት ልብ ላይ እሾክ ይተክላሉ፡፡ MYPAmh 135.7