መልዕክት ለወጣቶች

218/511

ግላዊ ሥራ

የክርስቶስ ሥራ በአብዛኛው ከግላዊ ቃለ መጠይቆች የተሰራ ነው፡፡ ለአንድ ነፍስ እንኳን ታማኝ አክብሮት ነበረው፡፡ ያ አንድ ነፍስ የተማረውን ትምህርት ለሺዎች ያደርሳል፡፡ MYPAmh 134.1

እጅግ የተሳካላቸው ሠራተኞች የሚባሉት እግዚአብሔርን በትናንሽ ነገሮች ለማገልገል የሚሠሩ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር በየግሉ ክር መሥራት፣ መረቡን በሚፈጥረው ልብስ ላይ መሸመንና ሥራውን መጨረስ አለበት፡፡ MYPAmh 134.2

ወጣቶች ወጣቶችን እንዲረዱ አስተምሩአቸው፡፡ ይህንን ለማድረግ በመሻት እያንዳንዱ ወጣት በሰፊው የሥራ መስክ የተቀደሰ ሰራተኛ ለመሆን የሚያበቃ የሥራ ልምድ ያገኛል፡፡ MYPAmh 134.3

እጅግ ቀላል በሆነ መንገድ በሺዎች የሚቆጠሩ ልቦችን ይደርሳሉ፡፡ እጅግ የተማሩ፣ እንደ የዓለም ታላላቆችና ተሰጥዖ ያላቸው ወንዶችና ሴቶች ተቆጥረው የታዩና የተሞገሱ ሰዎች እግዚአብሔርን በሚወድ፣ ስለዚህ ፍቅርም ዓለማውያን በተፈጥሮ በአእምሮአቸው ስለሚያሰላስሉአቸውና ስለሚመገቡአቸው ነገሮች እንደሚያወሩ በሚናገር ሰው እጅግ ትሁትና ቀላል ቃላት አእምሮአቸው ይታደሳል፡፡ ቃላት ምንም እንኳን በደንብ የተጠኑና የተዘጋጁም ቢሆኑ ያላቸው ተጽእኖ አነስተኛ ነው፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ልጆች እውነተኛና ታማኝነት ያለበት ሥራ በቃላት ወይም በአነስተኛ ነገሮች በማገልገል በተፈጥሮ ራስን ዝቅ በማድረግ ቢፈፀም ኖሮ ለብዙ ነፍሳት ለረዥም ጊዜ ተዘግቶ የኖረውን በር ይከፍት ነበር፡፡ Review and Herald, May 9, 1899. MYPAmh 134.4