መልዕክት ለወጣቶች

16/511

ሙሉ በሙሉ ራስን መስጠት

የክርስቶስ ኃይማኖት ማለት ያላችሁንን በሙሉ በፍፁም ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠትና ከመንፈስ ቅዱስ አመራር ጋር መስማማት ማለት ነው:: በመንፈስ ቅዱስ ሥጦታ አማካኝነት የግብረገብ ኃይል ይሰጣችሁና ለጌታ አገልግሎት ከዚህ በፊት የተሰጡአችሁ መክሊቶች ብቻ የሚኖሩአችሁ ሳይሆን የእነርሱ ብቃት በከፍተኛ ደረጃ ይበዛላችኋል:: ያሉንን ኃይሎች በሙሉ ለእግዚአብሔር አሳልፈን መስጠት የህይወትን ችግር በከፍተኛ ደረጃ ያቃልላል:: ከተፈጥሮ ልብ ስሜቶች ጋር የሚደረጉትን ትግሎች ሺህ ጊዜ ያዳክምና ያሳጥረዋል:: ኃይማኖት የወጣቶችንም ሆነ የአዛውንቶችን ነፍስ ከክርስቶስ ጋር የሚያስተሳስር ወርቃማ ገመድ ነው:: በእርሱ አማካይነት ፈቃደኛና ታዛዥ የሆኑት ጨለማና ውስብስብ በሆነው መንገድ አልፈው በሰላም ወደ እግዚአብሔር ከተማ ይደርሳሉ:: MYPAmh 27.4

ተራ የሆነ ችሎታ ብቻ ያላቸው ወጣቶች አሉ:: ሆኖም ከፍ ባለና ንፁህ መርህ በተነሳሱ መምህራን ሥር በመማርና በመገራት ሥልጠናውን ሲያጠናቅቁ እግዚአብሔር ለጠራቸው ታማኝነትን ለሚጠይቅ ሥራ ብቁ ሆነው መውጣት ይችላሉ:: ነገር ግን የተፈጥሮ ዝንባሌያቸውን ለማሸነፍ ፈቃደኛ ባለመሆናቸውና በቃሉ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ድምጽ ስለማይሰሙ የማይሳካላቸው ወጣቶች አሉ:: ነፍሳቸውን ከአደጋ አልተከላከሉም! ሥራቸውን በአደጋዎች ውስጥ ሆነው ለመሥራት ወስነዋል:: እነርሱ ልክ በአደገኛ ጉዞ ላይ ሆኖ ከአደጋው ለማምለጥ ምንም አይነት ምሪትና ትዕዛዝ እንደማይቀበልና በጥፋት አቅጣጫ እንደሚሄድ ሰው ናቸው:: MYPAmh 27.5