መልዕክት ለወጣቶች

15/511

ነፃነታችሁን አውጁ

እግዚአብሔር በርሱ ያመነ ሁሉ እንዳይጠፋ ግን የዘላለም ህይወት እንዲሆንለት አንድያ ልጁን አሳልፎ እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን ስለ ወደደ እርሱን ለማክበርና ማንኛውም ፈተና ወይም ጎናዊ ፍላጎት ወደ ኋላ እንዳይመልሳችሁ የህይወታችሁ ህግ አድርጉት:: እንደ ዳነ፣ ነፃ እንደሆነ የግብረገብ ወኪል ፣ ዘላለማዊ በሆነ ዋጋ እንደተዋጀ ሰው እግዚአብሔር ነፃነታችሁን እንድታውጁና እርሱ የሰጣችሁን ኃይሎች እንደ የሰማይ መንግስት ነፃ ተገዦች ስራ ላይ እንድታውሉት ይጠራችኋል:: በኃጢአት ቀንበር ሥር አትሁኑ ፣ ነገር ግን እንደ የነገስታት ንጉስ ተገዦች ለ•እርሱ ታማኝነታችሁን አረጋግጡ:: MYPAmh 27.2

በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ጌታ ለእናንተ ህይወትና ፀጋ በመስጠት ለተቀደሰ ኃላፊነት ብቁ እንዳደረጋችሁ አሳዩ:: በክፉ ኃይል ቁጥጥር ሥር መሆንን እምቢ በሉ:: እንደ ክርስቶስ ወታደሮች በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን ደህንነትን ፈልገን በማስተዋል መቀበል አለብን! ትክክለኛ መርሆዎችን መቀበልና መተግበር አለብን:: መለኮታዊው ጥበብ ለእግራችሁ መብራት መሆን አለበት:: ለራሳችሁና ለአምላካችሁ እውነተኛ (ታማኝ) ሁኑ:: የሚበጠር ነገር ሁሉ ይበጠራል:: ነገር ግን በእውነት ላይ ሥር ከሰደዳችሁና ከተመሰረታችሁ ከማይበጠሩ ነገሮች ጋር ትሆናላችሁ:: የእግዚአብሔር ህግ የፀናና የማይለወጥ ነው:: ህጉ የጅሆቫ የባህሪዩ መግለጫ ነው:: በቃላችሁም ሆነ በተጽእኖአችሁ በእርሱ ሥልጣን ላይ በትንሹም ቢሆን ውርደት እንዳታመጡ ወስኑ:: MYPAmh 27.3