መልዕክት ለወጣቶች
መዳረሻችሁን መምረጥ
እያንዳንዱ ሰው የራሱን መዳረሻ ወሳኝ መሆኑን ምነው ማወቅ በቻለ! በዚህ ህይወትም ሆነ በወደፊቱ ዘላለማዊ ህይወት የሚኖራችሁ ደስታ የሚወሰነው በእናንተው ነው:: ምርጫችሁ ከሆነ አሰተሳሰባችሁን፣ ቃላችሁንና ግብረገባችሁን የሚያረክሱ ጓደኞች ሊኖሩአችሁ ይችላል:: የምግብ ፍላጎታችሁንና የፍትወት ልጓማችሁን ልታላሉ ፣ ሥልጣንን ልትንቁ ፣ ሸካራ ቃላት ልትጠቀሙና ራሳችሁን እጅግ ዝቅ ወዳለው ደረጃ ልታወርዱ ትችላላችሁ:: ተጽዕኖአችሁ ሌሎችን የሚበክል ይሆንና ወደክርስቶስ ለምጣት ትችሉ ለነበራችሁት ነፍሳት መጥፊያ ምክንያት ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ ከክርስቶስ፣ ትክክለኛ ከሆነ ነገር፣ ከቅድስናና ከሰማይ ልታርቁአችው ትችላላችሁ:: በፍርድ ቀን የጠፉት ወደ እናንተ እያመለከቱ «በእርሱ ተጽእኖ ባይሆን ኖር ተሰናክዬ ኃይማኖትን ማፌዣ አላደርግም ነበር:: እርሱ ብርሃን ነበረው ፣ የሰማይን መንገድ ያውቅ ነበር:: እኔ ምንም ስለ ማላውቅ ተጨፍኜ ወደጥፋት መንገድ ሄድኩ::” ይላሉ:: ኦ! ለእንደዚህ አይነቱ ክስ ምን መልስ እንሰጥ ይሆን? እያንዳንዱ ግለሰብ ነፍሳትን ወዴት እየመራ እንደሆነ ማገናዘብ በጣም አስፈላጊ ነው:: ዘላለማዊ በሆነው ዓለም እይታ ውስጥ ነን:: ተጽእኖአችን የሚያስከፍለው ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ ተግተን መቁጠር አለብን፡፡ ዘላለማዊነትን ከስሌታችን ውስጥ ማስወጣት የለብንም፣ ነገር ግን ይህ የምሄድበት መንገድ እግዚአብሔርን ያስደስተዋልን? እያልን ራሳችንን ሁል ጊዜ የመጠየቅ ልምድ ሊኖረን ይገባል:: ትክክለኛ ለሆነው ነገር እጅግ ዝቅተኛ የሆነ ብርሃንና መረጃ ባላቸው ሰዎች አእምሮ የእኔ ተግባር እያሳደረ ያለው ተጽእኖ ምን ይሆን? MYPAmh 28.1