መልዕክት ለወጣቶች

203/511

መጽሐፍት ቅዱስና ሳይንስ

የብሉይና የአዲስ ኪዳን መጽሐፍትን በየቀኑ ማጥናት አስፈላጊ ነው፡፡ የእግዚአብሔር እውቀትና ጥበብ ሁል ጊዜ የእርሱን መንገዶችና ሥራዎች ለሚያጠና ተማሪ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ብርሃናችንና አስተማሪያችን መሆን አለበት፡፡ ወጣቶች እግዚአብሔር ጤዛን፣ ዝናብንና የፀሐይ ብርሃንን ከሰማይ በመላክ እጽዋት እንዲለመልሙ እንደሚያደርግ ማመን ሲማሩ፤ በረከቶች ሁሉ ከእርሱ እንደሚመጡና ውዳሴና ምስጋና ለእርሱ እንደሚገባው ሲገነዘቡ በመንገዳቸው በሙሉ እግዚአብሔርን ለመግለጥና ተግባራቸውን በታማኝነት ዕለት ከዕለት ወደ መፈፀም ይመራሉ፡፡ እግዚአብሔር በሐሳባቸው ሁሉ ውስጥ ይሆናል፡፡ MYPAmh 124.2

ብዙ ወጣቶች ስለ ሳይንስ ሲናገሩ ከተፃፈው በላይ ጠቢባን ናቸው፤ የእግዚአብሔርን መንገድና ሥራ የእነርሱን ውስን ግንዛቤ ሊገጥም በሚችል ነገር መግለጽ ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን ይህ አሳዛኝ ውድቀት ነው፡፡ እውነተኛ ሳይንስና የእግዚአብሔር ቃል ፍፁም ስምሙ ናቸው፡፡ ሐሰተኛ ሳይንስ ራሱን ከእግዚአብሔር የለየ ነው፤ ማስመሰል ያለበት ድንቁርና ነው፡፡ MYPAmh 124.3

እውቀት መሻትንና የሳይንስ ምርምርን ተከትለው ካሉ ታላላቅ ክፋቶች አንዱ በእነዚህ ምርምሮች ላይ የተሰማሩ ሰዎች ብዙ ጊዜ በንፁህና ባልተበከለ ኃይማኖት ውስጥ ያለውን የመለኮት ባሕርይ ማየት ይሳናቸዋል፡፡ የዓለም ጠቢባን የእግዚአብሔር መንፈስ በሰብዓዊ ልብ ላይ ያለውን ተጽዕኖ በሳይንሳዊ መርሆዎች ለማብራራት ሞክረዋል፡፡ በዚህ አቅጣጫ የሚደረግ ትንሹ እርምጃ አእምሮን ወደ ጥርጣሬ መረብ ይመራል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐይማኖት እግዚአብሔርን የመምሰል ምስጢር ነው፡፡ ማንኛውም ሰብዓዊ አእምሮ ሊያስተውለው አይችልም፤ ያልተለወጠ ልብም በፍፁም ሊያስተውለው ከሚችለው በላይ ነው፡፡ MYPAmh 124.4