መልዕክት ለወጣቶች
ከእግዚአብሔር የተማሩ
ወጣቶች ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ቀድሰው በመስጠታቸው አእምሮአቸው ደካማና ብቃት የጎደላቸው አይሆኑም፡፡ ለብዙዎች ትምህርት ማለት የመጽሐፍት እውቀት ነው፡፡ ነገር ግን «የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፡፡» እግዚአብሔርን የሚወድና የሚፈራ ትንሽ ህፃን እጅግ ችሎታ ያለውና የተማረ ሆኖ የግል ደህንነትን ጉዳይ ቸል ከሚል ሰው ይልቅ በእግዚአብሔር ዓይን ታላቅ ነው፡፡ ልባቸውንና ህይወታቸውን ለእግዚአብሔር ቀድሰው የሚሰጡ ወጣቶች ራሳቸውን የጥበብና የብቃት ሁሉ ምንጭ ከሆነው ጋር እያገናኙ ነው፡፡ MYPAmh 124.5
ዳንኤል እንዳደረገው ወጣቶች ከሰማያዊ መምህራቸው ቢማሩ ኖሮ የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት መሆኑን በርግጠኝነት ለራሳቸው ያውቁ ነበር፡፡ የፀና መሠረት ላይ ከተመሠረቱ በኋላ ልክ እንደ ዳንኤል እያንዳንዱን እድልና አጋጣሚ ለተሸለ ነገር በማዋል በእውቀት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ይደርሳሉ፡፡ ለእግዚአብሔር ተቀድሰውና የፀጋውን ጥበቃና የመንፈስ ቅዱስን የማነሳሳት ተጽእኖ በመያዝ ዓለማውያን ካላቸው የበለጠ የጠለቀ የአእምሮ ኃይል ይኖራቸዋል፡፡ MYPAmh 124.6
ሳይንስን ሰዎች በሚሰጡት ትርጉም መማር ማለት ሀሰተኛ ትምህርት መማር ማለት ነው፡፡ ከእግዚአብሔርና እርሱ ከላከው ከየሱስ ክርስቶስ መማር የመጽሐፍ ቅዱስን ሳይንስ መማር ነው፡፡ ልበ ንፁሆች በእያንዳንዱ ነገር፣ በእያንዳንዱ የትምህርት ክፍል እግዚአብሔርን ያያሉ፡፡ ከእግዚአብሔር ዙፋን የበራውን የመጀመሪያውን ብርሃን ሁኔታ ይገነዘባሉ፡፡ የመጀመሪያውን መንፈሳዊ እውቀት ብርሃን ለሚይዙ ከሰማይ ጋር ግንኙነት ይፈፀማል፡፡ MYPAmh 125.1
በእኛ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች እግዚአብሔርን ማወቅን ከማንኛውም ነገር በላይ አድርገው ማየት አለባቸው፡፡ ይህ እውቀት ሊገኝ የሚችለው መጽሐፍ ቅዱስን በመመርመር ብቻ ነው፡፡ «የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድነው ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው፡፡ የጠቢባንን ጥበብ አጠፋለሁ፤ የአስተዋዮችንም ማስተዋል እጥላለሁ ተብሎ ተፅፎአልና… ፡፡ ከሰው ጥበብ ይልቅ የእግዚአብሔር ሞችነት ይበልጣልና፣ የእግዚአብሔርም ድካም ከሰው ብርታት ይልቅ ይበረታልና፡፡ ነገር ግን እናንተ ከእግዚአብሔር ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው፡፡» 1ኛ ቆሮ 1፤ 18-31፡፡ The Youth’s Instructor .Nov.24,1903. MYPAmh 125.2