መልዕክት ለወጣቶች

202/511

እውነተኛ ጥበብ

ወጣት ወንዶችና ሴቶች ከፍተኛ ምድራዊ ትምህርት ቢኖራቸውም እንኳን የእግዚአብሔር መንግስት ተገዢዎች ሊያደርጉአቸው ለሚችሉአቸው ቀዳሚ መርሆዎች መሀይም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሰብዓዊ ትምህርት ማንንም ሰው ለሰማያዊ መንግስት ብቁ አያደርግም፡፡ የእግዚአብሔር መንግስት ተገዢዎች እንደዚያ የሆኑት በውጫዊ ቅርጽና አገልግሎቶች ወይንም መጽሐፍትን ለረጅም ጊዜ በማጥናት አይደለም፡፡ «የዘላለም ሕይወት ይህ ነው፤ እርሱም አንተን ብቻ እውነተኛ አምላክና አንተ የላከውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ነው፡፡” MYPAmh 124.1