መልዕክት ለወጣቶች

104/511

እንዴት ጠንካራ መሆን እንደሚቻል

ክርስቶስ ጠንካራ ሊያደረገን የሚችል እያንዳንዱን ሁኔታ አዘጋጅቶልናል። ሰላምና የይቅርታ ጣፋጭ ስሜት እንዲሰማን ክርስቶስ የሰጠንን ቃል ኪዳኖች ወደ አእምሮአችን ማምጣት ዋና ሥራው የሆነውን መንፈስ ቅዱስን ሰጥቶናል። ዓይኖቻችንን በአዳኝ ላይ ከተከልንና በእርሱ ኃይል ከታመንን የክርስቶስ ጽድቅ የእኛ ጽድቅ ስለሚሆንልን በደህንነት ስሜት እንሞላለን…። MYPAmh 73.1

ስለ እኛ የብቃት ማነስ ስናወራ እርሱን እናዋርደዋለን። ወደ ራሳችን ከመመልከት ይልቅ ያለ ማቋረጥ፣ በየእለቱ ወደ እርሱ አምሳያነት እየተለወጥን የበለጠ ስለ •እርሱ እየተነጋርን፣ ራሳችንን ለእርሱ ርህራሄና እርዳታ አሳልፈን ለመስጠት እየተዘጋጀን የተሰጡንን በረከቶች ለመቀበል ኢየሱስን እንመልከት። MYPAmh 73.2

ከእርሱ ጋር ግንኙነት በማድረግ ስንኖር ሳለ በእርሱ ጥንካሬ እየጠነከርን እንሄድና በዙሪያችን ላሉት ጠቃሚዎችና በረከት እንሆናለን። ጌታ እንድናደርግ እንደሚፈልግብን ብቻ ብናደርግ ኖሮ ልቦቻችን እንደ ቅዱስ በገና ይሆኑና እያንዳንዱ ምት የዓለምን ኃጢአት ለመቀበል ለተላከው አዳኝ ምሥጋናና ውዳሴ ያሰማ ነበር። MYPAmh 73.3