መልዕክት ለወጣቶች

103/511

እምነትና ተግባር

እምነት ስሜት አይደለም:: እምነት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ከራስ ወዳድነት ምንም ያልተሻለ የኃይማኖት መልክ አለ። ዓለማዊ ደስታ ያስደስተዋል። የክርስቶስን ኃይማኖት በማሰላሰል የረካና ስለሚያድን ኃይሉ ምንም የማያውቅ ነው። ይህንን ኃይማኖት የያዙ ሰዎች ኢየሱስን ስለማያውቁት ኃጢአትን አቅልለው ያዩታል። በዚህ ሁኔታ እያሉ ተግባርንም እጅግ አቅልለው ይገምቱታል። ነገር ግን ተግባርን በታማኝነት መፈፀም ለእግዚአብሔር ባሕሪይ ትክክለኛ ግምት ከመስጠት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ ይሄዳል። Review and Herald, February 28,1907. MYPAmh 72.4