መልዕክት ለወጣቶች
የእርሱን ግርማ ተመልከቱ
ፈተናዎች በርግጥም እንደሚያደርጉት ጥቃት ሲያደርሱባችሁ፣ ችግርና ግራ መጋባት ሲከባችሁ፣ ባዘናችሁና ተስፋ በቆረጣችሁ ጊዜ፣ ተስፋ ቆርጣችሁ ለመሸነፍ በተቃረባችሁ ሰዓት ባለፈው ጊዜ በእምነት ዓይን ብርሐን ወዳያችሁበት ተመልከቱ፣ ኦ ተመልከቱ! በዚህን ጊዜ ዙሪያችሁን ከቦ ያለው ጨለማ በእርሱ ግርማ ብሩህ ነፃብራቅ ይወገዳል። •ኃጢአት ነፍሳችሁን ለመቆጣጠር ሲታገላችሁና ህሊናችሁን ሲያጨናንቅ፣ አለማመን አእምሮአችሁን ሲያጨልመው ወደ አዳኙ ሂዱ። ፀጋውም ኃጢአትን ለማንበርከክ በቂ ነው። በእግዚአብሔር ደስ ያለንን ለማድረግ ይቅር ይለናል። MYPAmh 73.4
ከአሁን በኋላ ስለ ራሳችን ብቃት ማነስና ኃይል የለሽነት አናውራ። ከኋላችን ያሉ ነገሮችን በመርሳት በሰማይ መንገድ ወደ ፊት እንዘርጋ። በአግባቡ ጥቅም ላይ ብናውል በእግዚአብሔር አገልግሎት የበለጠ ጠቃሚ ሊያደርጉን የሚችሉትን መልካም አጋጣሚዎች ችላ አንበል። ያኔ እንደ ወርቅ ክሮች ቅድስና በሕይወታችን ውስጥ ያልፍና እኛ ራሳችንን ቀድሰን መስጠታችንን የሚመለከቱ መላእክት «ሰውን ከጠራ ወርቅ ይልቅ እጅግ የከበረ አደርጋለሁ፣ ከኦፊር ወርቅ ይልቅ አከብራለሁ::» የሚለውን ተስፋ ይደግሙታል። ደካማ፣ተሳሳች ሰዎች የእርሱን ሕይወት ለመኖር ራሳቸውን ለኢየሱስ አሳልፈው በሚሰጡበት ጊዜ ሰማይ በሞላ ይደሰታል። Review and Herald, October1,1908. MYPAmh 73.5