መልዕክት ለወጣቶች
የተገኘ ድል
የኃይል ሁሉ ምንጭ ከሆነው ጋር ስንገናኝ ሊኖረን ስለሚችለው ጥንካሬ ያለን ግምት በጣም ጥቂት ነው፡፡ በየጊዜው ወደ •ኃጢአት ስለምንወድቅ ሁል ጊዜም እንዲሁ መሆን እንዳለበት እናስባለን፡፡ በድክመቶቻችን ላይ ልክ እንደ አንድ ልንኮራበት እንደሚገባ ነገር ሙጭጭ እንላለን፡፡ ማሸነፍ ካለብን ፊታችንን እንደ ባልጩት ማጠንከር እንዳለብን ክርስቶስ ይነግረናል፡፡ እርሱ በአካሉ ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸክሞታል፡፡ እርሱ በሰጠን ኃይል እኛም ዓለምን ፣ ሥጋንና ሰይጣንን መቋቋም እንችላለን፡፡ እንግዲያውስ ስለ እኛ ድክመትና ብቃት ማነስ ከመናገር ይልቅ ስለ ክርስቶስ ብቃትና ጥንካሬ እናውራ፡፡ ስለ ሰይጣን ጥንካሬ ስናወራ ጠላት ኃይሉን በእኛ ላይ የበለጠ ያጠብቅብናል፡፡ ኃያል ስለ ሆነው ኃይል ስናወራ ጠላት ወደኋላ ያፈገፍጋል፡፡ ወደ እግዚኣብሔር ስንቀርብ እርሱም ወደ እኛ ይቀርባል፡፡ MYPAmh 72.1
ብዙዎቻችን የተሰጡንን መልካም ዕድሎች ሳናሻሽላቸው እንቀራለን፡፡ መልካም ለማድረግ ጥቂት ደካማ ጥረቶችን እናደርግና ወዲያውኑ ተመልሰን ወደ አሮጌ የኃጢኣት ሕይወት እንሄዳለን፡፡ ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት ካለብን የምንገባው ፍጹም በሆነ ባሕሪይ፣ እንከን ወይም የፊት መጨማደድ ወይም ማንኛውም ይህን የሚመስል ነገር ሳይኖርብን ነው፡፡ ወደ ጊዜው ማብቂያ ስንቃረብ ሰይጣን ተግቶ ይሰራል፡፡ አእምሮአችንን ለመቆጣጠር ለእኛ ሳይታይ ወጥመዶቹን ይዘረጋል፡፡ በሁሉም አቅጣጫ ከአእምሮአችን የእግዚአብሔርን ክብር ለመጋረድ ጥረት ያደርጋል፡፡ አእምሮአችንንና ልባችንን እርሱ እንዲቆጣጠር መፍቀድ ወይንም በታደሰችው ምድር ቦታ እንዲኖረንና የአብርሃም ምርጫ ባለ መብት የመሆን ውሳኔ ማድረግ የእኛ ጉዳይ ነው። MYPAmh 72.2
የእግዚአብሔር ኃይል ከሰብአዊ ጥረት ጋር በመጣመር ለእኛ ባለ ግርማ ድልን ሰርቶልናል። ይህንን አናደንቅምን? የሰማይ ብልፅግና በሙሉ በክርስቶስ ተሰጥቶናል። እግዚአብሔር ካደረገልን የበለጠ ማድረግ እንዲችል ከክፉ አባባል ጋር አንድነት መፍጠር አልነበረበትም። የፈጠራቸው ዓለማት፣ የሰማይ መላእክት ከዚህ የበለጠ ማድረግ እንደማይችል መመስከር ይችላሉ:: እግዚአብሔር እኛ እስካሁን ምንም የማናውቀው የኃይል ምንጭ ያለው ሲሆን በሚያስፈልገን ሰዓት ይህንን ኃይል ይሰጠናል። ነገር ግን ሁል ጊዜም የእኛ ጥረት ከመለኮታዊ ጋር መጣመር አለበት። የአእምሮ ችሎታችን፣ የግንዛቤ ኃይላችንና የአካል ብርታታችን ለተግባር መነሳሳት አለበት። ለአደጋ ጊዜ የምንነሣ ከሆንንና ጌታቸውን እንደሚጠብቁ ሰዎች ራሳችንን ካስታጠቅን በባሕሪያችን ያለውንእያንዳንዱን ድክመት ለማሸነፍ ከሠራን እግዚአብሔር የበለጠ ብርሃን፣ ጥንካሬና እርዳታ ይሰጠናል። The Youth’s Instructor, January 4, 1900. MYPAmh 72.3