መልዕክት ለወጣቶች
የእድሜ ልክ ተጋድሎ (ተቃርኖ)
ፈሪ እርግብን የሚያሳድደውን ጭልፊት አይታችሁ ታውቃላችሁን? ጭልፊቱ ግዳዩን ለመያዝ እርግቡ ከሚበረው ከፍታ አልፎ ከፍ ብሎ እንደሚበር ለእርግቦቹ ተፈጥሮ አስተምሮአቸዋል፡፡ ስለዚህ እርግብዋ ጭልፊቶች በርረው ከሚያውቁበት ከፍታ በላይ ከፍ ብላ በሰማይ ሰማያዊ ቅንፍ ውስጥ ትበርራለች፡፡ ነገር ግን ይህ ጥረትዋ ከንቱ ነው፡፡ እርግብዋ ምንም ነገር ከመብረር እንዲያግዳት ወይም ወደ ምድር እንዲስባት እስካልፈቀደች ድረስ ከአደጋ ነፃ ነች፡፡ ነገር ግን ለአንድ አፍታ እንኳን ተደናቅፋ ዝቅ ብላ ብትበር ያ ነቅቶ የሚጠብቀው ጠላትዋ በፍጥነት ወደ ታች በግዳዩ ላይ ይበራል፡፡ ያቺ ምስኪን እርግብ የዚያ ጨካኝ ጭልፊት ግዳይ ሆና ስትወድቅ ማየት እንዴት ያሳዝናል! MYPAmh 70.6
ከፊታችን ጦርነት ይጠብቀናል፡፡ ጦርነቱ ከሰይጣንና ከአታላይ ፈተናዎቹ ጋር የሚደረግ የእድሜ ልክ ጦርነት ነው፡፡ ጠላት ነፍስን ለማጥመድ እያንዳንዱን ክርክርና ማታለያ ይጠቀማል፡፡ የሕይወትን አክሊል ለማግኘት ልባዊና የማያቋርጥ ጥረት ማድረግ አለብን፡፡ በአዳኛችን ድል ማግኘት እስክንችልና ጦርነቱን በድል እስክንወጣ ድረስ የጦር መሳሪያችንን መጣል ወይንም ከጦር ሜዳው መውጣት የለብንም፡፡ የእምነታችን ጀማሪና ፈፃሚ በሆነው ላይ ዓይናችንን ተክለን እስከቆየን ድረስ አደጋ አይደርስብንም፡፡ ፍቅራችን በምድራዊ ነገሮች ላይ ሳይሆን በላይ ባሉ ነገሮች ላይ መሆን አለበት:: የክርስቶስን ፀጋዎች ለማግኘት በእምነት ከፍ እያልን አሁንም ወደ ከፍታው መነሳት አለብን:: ወደር የለሽ የሆነውን ውበቱን በየእለቱ እያሰላሰልን የበለጠ ወደ እርሱ ባለ ግርማ ምስል ማደግ አለብን:: ከሰማይ ጋር ግንኙነት ፈጥረን ስንኖር ሰይጣን እኛን ለማጥመድ መረቡን በከንቱ ይጥላል፡፡ The Youth’s Instructor, May 12, 1898. MYPAmh 71.1