መልዕክት ለወጣቶች
የህይወት ንጽህና በሁኔታዎች አይወሰንም
በጣም ምቹ ባልሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ፍፁም የክርስትና ህይወትን ከክርስቶስ በተሻለ ሁኔታ ለመኖር ማንም ሰው አይጠራም፡፡ «ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን » በማለት በሚደነቁበት በናዝሬት ከተማ ክርስቶስ ለሰላሣ ዓመታት መኖሩ ዛሬ የኃይማኖት ልምምዳቸው ከሁኔታዎች ጋር መጣጣም ወይም መስማማት አለበት ለሚሉ ወጣቶች ዘለፋ ነው፡፡ ወጣቶች ዙሪያቸው መጥፎና ደስ የማይል ሲሆን ፍፁም የሆነ ክርስቲያናዊ ህይወት ላለመኖራቸው ምክንያት ያቀርባሉ፡፡ የክርስቶስ ምሳሌነት የርሱ ተከታዮች እንከን የለሽ ሕይወት ለመኖር ቦታ፣ ብልጽጋና ወይም መልካም እድል ይወስናቸዋል ለሚለው ሃሳብ ዘለፋ ነው፡፡ የእግዚአብሔር በጎነት ከጠራቸው የእነርሱ ታማኝነት ማንኛውንም ቦታም ሆነ ሥልጣን፣ ዝቅተኛም ቢሆን፣ የተከበረ እንደሚያደርግላቸው ያስተምራቸዋል፡፡ MYPAmh 57.4
የክርስቶስ ህይወት ንጽህና፣ መረጋጋትና የዓላማ ፅናት ከችግር፣ ከድህነትና ከአደጋ ነፃ በሆነ ሕይወት ላይ የሚደገፍ አለመሆኑን ለማሳየት የታቀደ ነበር፡፡ ብዙ ወጣቶች የሚያማርሩትን ፈተናና ብቸኝነት ክርስቶስ ያለ አንዳች ማጉረምረም ተቀበላቸው፡፡ ለወጣቶች የሚያስፈልገው ብቸኛ ልምምድ ይህ ነው፡፡ ይህ ልምምድ የባሕርይ ጽናትን ይሰጣቸውና እንደ ክርስቶስ ፈተናን ለመቋቋም በመንፈስ ጠንካሮች ያደርጋቸዋል፡፡ ራሳቸውን ከትክክለኛ አቅጣጫ ከሚያስቱአቸውና የሞራል እርኩሰት ከሚያመጡባቸው ነገሮች ቢለዩ በሰይጣን ወጥመዶች አይሸነፉም፡፡ በየዕለቱ ወደ እግዚአብሔር በመፀለይ ፈተናዎችንና የሕይወትን ጽኑ እውነታዎች ለመሸከምና አሸናፊዎች ሆነው ለመውጣት ጥበብና ፀጋ ያገኛሉ፡፡ ታማኝነትና ጤናማ አእምሮ ሊጠበቁ የሚችሉት ነቅቶ በመጠበቅና በመፀለይ ነው፡፡ የክርስቶስ ሕይወት በስድብ፣ በንቀትና በድህነት ወይም በችግሮች ምክንያት እንዲደክም ያልተፈቀደ የትጉህ ጥረት ምሳሌ ነው፡፡ MYPAmh 57.5
ከወጣቶችም የሚጠበቀው ይህ ነው፡፡ ፈተናዎች ቢበዙባቸው እግዚአብሔር እየፈተናቸውና ታማኝነታቸውን •እያረጋገጠ እንደሆነ ያውቃሉ፡፡ እስከዚህ ደረጃ ድረስ ተስፋ አስቆራጭ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ የባሕርይ ንጽህናቸውን ቢጠብቁ ድፍረታቸው፣ ጽናታቸውና የመታገስ ኃይላቸው ይጨምርና በመንፈስ እየጠነከሩ ይሄዳሉ፡፡ The Youth’s Instructor March 1872. MYPAmh 58.1