መልዕክት ለወጣቶች
በተቃርኖ ውስጥ የባህሪይ ጥንካሬ
የክርስቶስ የመጀመሪያዎቹ ሰላሳ አመታት ያለፉት ድብቅ በሆነው የናዝሬት መንደር ነበር፡፡ የዚህ መንደር ነዋሪዎች በክፉነታቸው የታወቁ ነበሩ፡፡ በዚህም ምክንያት ነበር ናትናኤል «ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን?» ብሎ የጠየቀው፡፡ ስለ ክርስቶስ የመጀመሪያው ሕይወቱ ወንጌላውያን ብዙ አይነግሩንም ፡፡ ስለ እርሱ የልጅነት ሕይወት ተጠቅሶ የምናገኘው ከወላጆቹ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም መሄዱን የሚገልጽ አጭር መግለጫና «ህፃኑም አደገ፣ በመንፈስም ጠነከረ፣ ጥበብም ተሞልቶ ነበር፣ የእግዚአብሔር ፀጋም በላዩ ነበር፡፡” የሚለውን ብቻ ነው፡፡ MYPAmh 57.1
ክርስቶስ በሁሉም ነገር ምሳሌያችን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ፈቃድ የልጅነት እድሜውን ያሳለፈው በናዝሬት ከተማ ሲሆን ሕይወቱ ሁል ጊዜ ለፈተና የተጋለጠ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት በኃጢአትና በክፋት መካከል ንፁህና እንከን የለሽ ሆኖ ለመቆየት ሁል ጊዜ መጠበቅ ነበረበት፡፡ ይህንን ቦታ የመረጠው ክርስቶስ ራሱ አልነበረም፡፡ ፀባዩ በተለያየ መንገድ ተፈትኖ እንዲሞከር ይህንን ቦታ የመረጠለት የሰማይ አባቱ ነበር:: ለልጆች፣ ለወጣቶችና በእድሜ ለበሰሉ ሰዎች ፍፁም ምሳሌ መሆን እንዲችል የክርስቶስ የልጅነት ጊዜ ሕይወቱ ለከባድ ፈተናዎች፣ መከራዎችና ግጭቶች የተጋለጠ ነበር፡፡ MYPAmh 57.2
ብዙ ጊዜ ልጆችና ወጣቶች ለክርስትና ህይወት ምቹ ባልሆነ አካባቢ ይሆኑና በቀላሉ ለፈተናዎች ይሸነፋሉ፡፡ ይህንን የኃጢአት መንገድ ለመከተላቸው የአካባቢያቸውን ምቹ አለመሆን እንደ ምክንያት ያቀርባሉ፡፡ ክርስቶስ በሥራ ላይ በማሳለፍና እጆቹን በስራ እንዲጠመዱ በማድረግ ፈተናን ወደራሱ አልጋበዘም፡፡ ነገር ግን ባሕርያቸው ክፉ ከሆኑት ራሱን አገለለ፡፡ ወደ ፊት ልጆችና ወጣቶች •እንዲሄዱበት ሊጠሩ በሚችሉበት ባልተስተካከለ አስቸጋሪ መንገድ ላይ እግሩን አሳረፈ፡፡ ለራሱ የብልጽግናንና የስንፍናን መንገድ አልመረጠም፡፡ ወላጆቹ ድሆች ነበሩ፡፡ ኑሮአቸውን ይገፉ የነበሩት በየቀኑ በሚያደርጉት የሥራ ጥረት ነበር፡፡ ስለዚህ የክርስቶስ ሕይወት የድህነት፣ ራስን የመካድና የብቸኝነት ነበር፡፡ ከወላጆቹ ጋር የእነርሱን ተግቶ የመስራት ሕይወት ተጋራ፡፡ MYPAmh 57.3