መልዕክት ለወጣቶች
ሰማያዊ አእምሮ ያለው የመሆን አስፈላጊነት
የእግዚአብሔርን ቃል አማካሪያችን ስናደርግና ብርሃንን ለማግኘት ቃሉን ስንመረምር የእግዚአብሔር መላእክት አእምሮን ለማንቃትና እንድናስተውል ለማድረግ አጠገባችን ይመጣሉ። ያኔ “የቃላቶችህ መግቢያ ብርሃን ይሰጣል! ላልተማሩትም እውቀት ይሰጣቸዋል።” የተባለው እውነት ይሆናል። ክርስቲያኖች ነን በሚሉ ወጣቶች መካከል ለእግዚአብሔር ቃል የተሰጠው ትኩረት እጅግ አናሣ ከመሆኑ የተነሣ ሰማያዊ አእምሮ ያላቸው ጥቂት መሆናቸው የሚያስደንቅ አይደለም። መለኮታዊ ምክሮች ተሰሚነት አላገኙም! ተግሳፆች ተቀባይነት አላገኙም! ያለፉ ኃጢአቶችን ለመተውና እያንዳንዱን የእርኩሰት እድፍ በማንፃት ፀጋና ሰማያዊ ጥበብ አልተፈለጉም። የዳዊት ፀሎት «የቃልህን መንገድ እንዳስተውል እርዳኝ! ያኔ ያንተን አስደናቂ ሥራዎች አወራለሁ::” የሚል ነበር። MYPAmh 270.5
ወጣቶቻችንና በእድሜ የበሰሉ ሰዎች አንድነት በሚፈጥሩበት ጊዜ ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ ቢመሩ ኖሮ ንግግራቸው በከበሩ ነገሮች ላይ ይሆን ነበር። አእምሮ ንፁህ ሲሆንና ሐሳቦች በእግዚአብሔር እውነት ከፍ ከፍ ሲሉ ቃላቶችም ተመሳሳይ ባሕርይ ይኖራቸዋል። “በብር ጽለል ላይ እንዳሉ እንደ ወርቅ እንኳዮች” ይሆናሉ። ነገር ግን አሁን ባለው ማስተዋልና ልምምድ፣ ክርስቲያን ነን ባዮች እንኳን ረክተው በተቀመጡበት ዝቅተኛ ደረጃ የሚሰማው ንግግር ርካሽና ትርፍ የለሽ ነው። “ከምድር ምድራዊ” ነው። በመሆኑም የእውነት ወይም የሰማይ ሽታ ስለሌለው የተማሩ ዓለማውያን ወዳሉበት ደረጃ እንኳን መድረስ አይችልም። MYPAmh 271.1