መልዕክት ለወጣቶች

468/511

ቅድስና የማይቋረጥ ሂደት

ክርስቶስና ሰማይ ዋና የማሰላሰል ሐሳቦች ሲሆኑ ንግግርም ያንኑ እውነታ ያረጋግጣል። ንግግር በጨው የተቀመመ ይሆናል! ተናጋሪው በመለኮታዊ ት/ቤት ከመለኮታዊው መምህር እየተማረ የነበረ መሆኑን ይገልጣል። ዘማሪው “የእውነትን መንገድ መርጫለሁ፣ ፍርዶችህንም በፊቴ አስቀመጥኋቸው» ይላል፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ከበረ ሀብት በልቡ ውስጥ ደበቀው። ቸል ለመባል ሳይሆን በሕይወቱ እንዲለማመድ ወደ አእምሮው መግቢያ አገኘ። MYPAmh 271.2

በየዕለቱ፣ በየሰዓቱ በውስጣችን የማያቋርጥ ራስን የመካድና የመቀደስ ሂደት መኖር አለበት። ያኔ የውጭ ተግባሮቻችን ኢየሱስ በእምነት በልብ ውስጥ ማደሩን ይገልጣሉ። ቅድስና ነፍስ እውቀትን የምታገኝባቸውን መንገዶች አይዘጋም፣ ነገር ግን አእምሮን በማስፋት እውነትን እንደተደበቀ ሀብት እንዲሻ ያነሳሳል። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ ደግሞ የቅድስና ሥራን ያፋጥናል። ሰማይ አለ፣ ወደዚያ ለመድረስ ምን ያህል ከልባችን ጥረት እያደረግን ነን! MYPAmh 271.3

በትምህርት ቤቶቻችንና በከፍተኛ የትምህርት ተቋሞቻችን ያላችሁ ተማሪዎች ኢየሱስን እንደ አዳኛችሁ እንድታምኑበት እማፀናችኋለሁ። ከእውነተኛ ልባችሁ ወደ እርሱ ስትመጡ በፀጋው ሊረዳችሁ ዝግጁ መሆኑን እመኑ:: መልካሙን የእምነት ገድል መጋደል አለባችሁ። የህይወትን አክሊል ለማግኘት መታገል አለባችሁ:: ሰይጣን በመዳፉ ውስጥ ሊያደርጋችሁ እየፈለገ ስለሆነ ለማምለጥ ጥረት አድርጉ። ራሳችሁን ከእርሱ እጅ መንጭቃችሁ ከላወጣችሁ በቀር ሽባ ትሆኑና ትጠፋላችሁ። ጠላታችሁ በቀኛችሁና በግራችሁ፣ በፊታችሁና በኋላችሁ ነው! ከእግራችሁ በታች ልትረግጡት ይገባል። ማግኘት የሚገባችሁ ዘውድ ስላለ ለማግኘት ጥረት አድርጉ። ይህንን ዘውድ ማግኘት ካልቻላችሁ በዚህ ሕይወትም ሆነ በወደፊቱ ሕይወት ሁሉንም ነገር ስለምታጡ ተጋዶሉ። ተጋደሉ፣ ግን መጋደላችሁ ከሞት በተነሳው አዳኛችሁ ብርታት ይሁን።r.—The Review and Herald, August 21, 1888. See also Fundamentals of Christian Education, 129-137 MYPAmh 271.4