መልዕክት ለወጣቶች

425/511

ጉዳት የማያስከትሉ መዝናኛዎችን አቅርቡ

ወጣቶች በሽምግልና እድሜ የሚታዩ ጭምትነትና እርጋታ ሊኖራቸው አይችልም! ልጅም እንደ አዛውንት ዝምተኛ ሊሆን አይችልም። ወደ ኃጢአት የሚመሩ መደሰቻዎች መወገዝ እንዳለባቸው የሚታወቅ ቢሆንም ወላጆች፣ መምህራንና አሳዳጊዎች የወጣቶቹን ግብረ ገብ የማይበክሉና የማያበላሹ ጉዳት የሌላቸውን መደሰቻዎች ማቅረብ አለባቸው። ወጣቶቹ እንደተጨቆኑ ተሰምቶአቸው ከቁጥጥራችሁ ሥር ወጥተው ወደ ሞኝነትና ወደ ጥፋት እንዲፈረጥጡ በሚያደርጉ ግትር ህጎችና ገደቦች አትሰሩአቸው። ፅኑ፣ ርህሩህና አዛኝ በሆኑ እጆች አእምሮአቸውንና ተግባራቸውን በመቆጣጠር አስተዳድሩ! ሆኖም አሁንም ለእነርሱ ከሁሉ የተሻለ መልካም እንደምታስቡላቸው እንዲገነዘቡ በጨዋነት፣ በጥበብና በፍቅር አድርጉት:: Counsels to Teacher, Parents and Students, P. 335. MYPAmh 245.1