መልዕክት ለወጣቶች

386/511

ባሕርይን የሚገነቡ ነገሮች

ልጆችና ወጣቶች ቃላቶቻቸውንና ተግባራቸውን እንዲጠብቁ ማሰልጠን አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ተግባሮቻቸው ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን እነርሱ ግንኙነት ለሚፈጥሩአቸው ሁሉ የፀሐይን ብርሐን ወይም ጥላን ሊያስከትል ስለሚችል ነው፡፡ ነገር ግን ወጣቶች ጥንቁቆች፣ አሳቢዎችና ክፉ ከሚመስል ነገር ሁሉ የራቁ ከመሆናቸው በፊት ከላይ የሚመጣውን ጥበብና ኢየሱስ ብቻ መስጠት የሚችለውን ብርታት ሊያገኙ ይገባል…፡፡ MYPAmh 224.1