መልዕክት ለወጣቶች
እውነተኛ ውበት
ብዙ ሰዎች ውበትና ያማረ ልብስ በዓለም ውስጥ ተቀባይነት እንደሚያስገኝላቸው በማሰብ ራሳቸውን ያታልላሉ፡፡ ነገር ግን በውጫዊ አለባበስ ብቻ የሚታይ ውበት ጥልቀት የሌለውና የሚቀየር ነው፡፡ በእነዚህ ነገሮች ላይ መደገፍ አይቻልም፡፡ ክርስቶስ ለተከታዮቹ የሚሰጠው ውበት በፍጹም አይጠፋም፡፡ እርሱ «ለእናንተም ጸጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይንም ልብስን በመጎናጸፍ፣ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ» ይላል፡፡ MYPAmh 224.2
ወጣቶች ራሳቸውን በውጫዊ ሁኔታ ማራኪ ለማድረግ ከሚያጠፉት ሰዓት ግማሹ እንኳን ነፍስን ለመግራትና ለውስጣዊ ውበት ቢውል ኖሮ በባሕርያቸው፣ በቃላቶቻቸውና በድርጊቶቻቸው ምንኛ ልዩነት በታየ ነበር፡፡ ክርስቶስን በእውነት መከተል የሚፈልጉ ሰዎች በአለባበስ ሁኔታቸው ጥንቃቄ ያደርጋሉ፡፡ MYPAmh 224.3
በአለባበስ ላይ ያለ መጠን እየባከነ ያለ ገንዘብ የእግዚአብሔርን ሥራ ወደ ፊት እንዲቀጥል ለማድረግና አእምሮአቸው ውስጥ ጠቃሚ የሆነ እውቀትን ለማጠራቀም ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ በዚህ ሁኔታ ራሳቸውን ታማኝነትን ለሚጠይቅ ቦታ ያዘጋጃሉ፡፡ ወሰን የለሽ ዋጋ በመክፈል የገዛቸው ኢየሱስ የሚጠብቅባቸውን ነገር መፈጸም ይችላሉ፡፡ MYPAmh 224.4
ውድ ልጆችና ወጣቶች፣ ኢየሱስ እርሱን ለሚወዱና ለሚያገለግሉ ያዘጋጀላቸውን ቤት ሊሰጣችሁ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል፡፡ እርሱ ሰማያዊውን ቤት በመተው በኃጢአት ወደ ተበከለው ዓለም መጣ፡፡ MYPAmh 224.5
ላደረገላቸው ነገር አድናቆት ወደ ሌላቸው፣ የእርሱን ንጽህናና ቅድስና ወደ ማይወዱ፣ ትምህርቱን ወዳጣጣሉና በመጨረሻም እጅግ ጭካኔ በተሞላበት ሞት ወደ ገደሉት ሕዝብ መጣ፡፡ በእርሱ ያመነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲሆንለት እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን አሳልፎ እስከሚሰጥ ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዷልና፡፡ MYPAmh 224.6