መልዕክት ለወጣቶች

358/511

የጠቃሚነት ክፍት በሮች

ለሌሎች ጠቃሚ ልንሆን የምንችልባቸው ሺህ በሮች በፊታችን ተከፍተዋል:: ብዙ ጊዜ በቂ ገንዘብ ባለመኖሩ እናላዝናለን፣ ነገር ግን ክርስቲያኖች ከልባቸው የተዘጋጁ ቢሆኑ ኖሮ ገንዘባቸውን ሺህ እጥፍ ያበዙት ነበር። ለሌሎች ጠቃሚዎች መሆን የምንችልባቸውን መንገድ የሚዘጋ እራስ ወዳድነት፣ ራስን በማስደሰት መጠመድ ነው። MYPAmh 206.3

ለተሻለ ጥቅም ማዋል ስንችል ሀሳብን፣ ጊዜንና ጉልበትን ለሚይዙ ተራ ጣዖቶች እየወጣ ያለው ገንዘብ ምንኛ ብዙ ነው! ውድ በሆኑ ቤቶችና ቁሳቁሶች፣ የራስ ደስታን በመፈለግ፣ ለቅንጦት በተዘጋጀና ባልተመጣጠነ ምግብና ጎጂ በሆኑ ተግባራት ላይ ምን ያህል ገንዘብ እየባከነ ነው! ማንንም በማይጠቅሙ ስጦታዎች እየባከነ ያለ ገንዘብ ምን ያህል ነው! ዛሬ ክርስቲያን ነን ባዮች ነፍሳትን ከፈታኙ ለማዳን ከሚያወጡት የበለጠ፣ እጅግ ብዙ እጥፍ የሚበልጥ ገንዘብ ለማይጠቅሙና ብዙ ጊዜ ጎጂ ለሆኑ ነገሮች እያወጡ ናቸው። MYPAmh 206.4

ብዙ ክርስቲያን ነን ባዮች የሌሎችን ፍላጎት ለማሟላት ምንም ነገር ማትረፍ እስከማይችሉ ድረስ እጅግ ብዙ ገንዘብ ለልብስ ወጪ ያደርጋሉ። ተራ የሆነውን ልብስ እንኳን በመከራ የሚያገኙትን ችላ በማለት ለራሳቸው ውድ ጌጣጌጦችና ልብሶች ሊኖራቸው እንዲሚገባ ያስባሉ። MYPAmh 206.5