መልዕክት ለወጣቶች
ትርፍራፊውን መሰብሰብ
ውድ እህቶቼ ሆይ የአለባበስ ሁኔታችሁን በመጽሐፍ ቅዱስ ከተሰጡት ህጎች ጋር ብታጣጥሙት ኖሮ ደሃ እህቶቻችሁን የምትረዱበት እጅግ ብዙ ነገር ይኖራችሁ ነበር። ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ጊዜም ይኖራችኋል:: አብዛኛውን ጊዜ ይህ በጣም ይፈለጋል። እናንተ በአስተያየታችሁ፣ በብልሃቶቻችሁና በሙያችሁ ልትረዷቸው የምትችሏቸው ብዙዎች አሉ። ቀላል ሆኖ የሚስብ አለባበስን አሳዩአቸው። ብዙ ሴቶች ከእግዚአብሔር ቤት የሚርቁበት ምክንያት የራሳቸውን መናኛና የማይገጥም ልብስን ከሌሎች ሴቶች ልብስ ጋር በማወዳደር ነው። ከዚህ ንፅፅር የተነሳ በቀላሉ የሚነካ መንፈስ ያላቸው ብዙዎች መራር የሆነ የበታችነትና ኢፍትሃዊነት ስሜት ይሰማቸዋል። ከዚህም የተነሳ ብዙዎች የኃይማኖትን እርግጠኝነት በመጠራጠር ልባቸውን ለወንጌል ወደ ማደንደን ተመርተዋል። MYPAmh 206.6
ኢየሱስ “ምንም ነገር እንዳይባክን ትርፍራፊውን ሰብስቡ” ይለናል። በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ በረሃብ፣ በደም መፍሰስ፣ በቃጠሎና በመቅሰፍቶች እየጠፉ እያሉ የሰው ዘር ወዳድ የሆነ ሁሉ መሰሎቹን ለመጥቀም ምንም ነገር እንዳይባክንና አላስፈላጊ ወጪ እንዳይሆን መጠበቅ አለበት። MYPAmh 206.7
ጊዜያችንንም ሆነ አስተሳሰባችንን ማባከን ስህተት ነው:: ለራሳችን ክብር የምንሰዋትን እያንዳንዷን ደቂቃ እያበከንናት ነን። እያንዳንዷ ደቂቃ ዋጋ ቢሰጣትና በትክክል ስራ ላይ ብትውል ኖሮ ለራሳችንም ሆነ ለዓለም ማድረግ ለምንፈልገው ነገር ሁሉ ጊዜ ይኖረን ነበር። በእያንዳንዱ የገንዘብ አወጣጥ፣ በጊዜ፣ በጉልበትና በአጋጣሚዎች አጠቃቀም እያንዳንዱ ክርስቲያን ለአመራር ወደ እግዚአብሔር ይመልከት። “ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጎድለው ሳይቆጥብ ለሁሉም በልግስና የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፣ ይሰጠዋልም::” Ministry of Healing, P. 206-208. MYPAmh 207.1