መልዕክት ለወጣቶች

357/511

ቁጠባና ልግስና

ብዙ ሰዎች ቁጠባን ከስስትና ከጠባብነት ጋር በማምታታት ንቀዋል። ነገር ግን ቁጠባ ሰፋ ካለው ልግስና ጋር አብሮ የሚሄድ ነው ። በርግጥ ያለ ቁጠባ እውነተኛ ልግስና የለም። ለመስጠት መቆጠብ አለብን ። MYPAmh 206.1

ማንም ሰው ራሱን ካልካደ በስተቀር እውነተኛ ልግስና መለማመድ አይችልም:: እንደ ክርስቶስ ወኪሎች የተሰጠንን ስራ መፈፀም የምንችለው በትህትና ሕይወት፣ ራስን በመካድና ጥብቅ ቁጠባ በመለማመድ ብቻ ነው። ኩራትና አለማዊ ፍላጎት ከልቦቻችን መወገድ አለባቸው። በሥራችን ሁሉ በክርስቶስ ሕይወት ተገልጦ የነበረው ራስን ያለመውደድ መርሕ መተግበር አለበት። በቤቶቻችን ግድግዳዎች የሚደረጉ ፎቶዎችና ማስጌጫዎች «ከቤትህ የጠፉትን ምስኪኖች አምጣቸው” ብለን የምናነባቸው መሆን አለባቸው:: በልብሶቻችን ዘርፍ በእግዚአብሔር ጣት እንደተፃፈ ሆኖ “የተራቆቱትን አልብሱ” የሚል ጽሁፍ መታየት አለበት፡፡ በወጥ ቤታችን ውስጥ በምግብ በተጨናነቀው ጠረጴዛችን ላይ “እንጀራህን ለተራቡ ትሰጥ ዘንድ አይደለምን?” የሚል ጽሁፍ ማየት አለብን። MYPAmh 206.2