መልዕክት ለወጣቶች
ራስን የመካድ ስራ
ከቤት ወደ ቤት በመሄድ ብዙ ፎቶግራፎችን ካየሁ በኋላ ህዝባችንን ስለዚህ ክፋት እንዳስጠነቅቅ መመሪያ ተሰጥቶኛል። MYPAmh 205.2
ለእግዚአብሔር ይህን ያህል ማድረግ እንችላለን። እነዚህን የፎቶግራፍ ጣዖቶችን ከእይታ ማስወገድ እንችላለን። ለጥሩ ነገር የሚሆን ኃይል የላቸውም፣ ነገር ግን በእግዚአብሔርና በነፍስ መካከል ጣልቃ ይገባሉ። የእውነትን ዘሮች ለመዝራት ምንም አይፈይዱም:: ክርስቶስ •እርሱን እንከተላለን የሚሉትን ሰዎች የእግዚአብሔርን ሙሉ እቃ ጦር እንዲለብሱ ይጠራቸዋል። MYPAmh 205.3
የትምህርት ተቋሞቻችን የመንፈስ ቅዱስ የማደስ ኃይል ሊሰማቸው ያስፈልጋል። “ጨው ጣእሙን ካጣ ለምን ይጠቅማል? ከዚያ በኋላ ለምንም አይጠቅምም፣ ነገር ግን ወደ ውጪ ይጣልና በሰዎች ይረገጣል።” በትምህርት ቤቶቻችንና በጤና ተቋሞቻችን በመምህርነት ሥራ ተሰማርተው ያሉ ከፍ ወዳለው የቅድስና ደረጃ መድረስ አለባቸው። በእነዚህ ተቋማት እየተማሩ ያሉና ራሳቸውን ለሚስዮናዊ ስራ እያዘጋጁ ያሉ ሁሉ ራስን መካድን ለመተግበር መማር አለባቸው። MYPAmh 205.4
እኛ የእግዚአብሔር መጋቢዎች ነን። “ከመጋቢዎችም ታማኝ ሆኖ መገኘት ይጠበቅባቸዋል።” እግዚአብሔር የሰጠንን ገንዘብ በጥንቃቄ መያዝ ያስፈልጋል። እርሱ ሲመጣ የእርሱ የሆነውን ከትርፍ ጋር ለመመለስ የተሰጡንን መክሊቶች በተቻለ መጠን በጥሩ ስራ ላይ በማዋል ብቃታችንን መሳደግ ያስፈልጋል።.—The Review and Herald, June 13, 1907. በተደጋጋሚ ፎቶዎችን መነሳት MYPAmh 205.5
የወጣቶች ልብ በራስ ፍቅር ተሞልቷል። ፊቶቻቸው በአርቲስት ተሰርቶ ማየትን በፍላጎታቸው ያሳያሉ፣ አንዴ በተነሱት ፎቶ አይረኩም፣ ነገር ግን የኋለኛው ከፊተኛው በጥራት የተሻለ እንደሚሆን ተስፋ በማድረግና ከመጀመሪያው የበለጠ የተዋበ ሆኖ ለመገኘት በመፈለግ በተደጋጋሚ ፎቶ ይነሳሉ። በዚህ መንገድ የጌታ ገንዘብ ባክኖአል። ይህንን በማድርግ የተገኘው ትርፍ ምንድነው? Testimonies for the church, volume1 P 500. MYPAmh 205.6