መልዕክት ለወጣቶች
የሙዚቃ ጥቅሞች
ሙዚቃ የተፈጠረው ቅዱስ ተግባርን ለመፈፀም፣ አስተሳሰባችንን ንፁህ ወደ ሆነው፣ ወደ ከበረውና ከፍ ከፍ ወደሚያደርገው ለማንሳት፣ በነፍስ ውስጥ ለእግዚአብሔር ራስን ቀድሶ መስጠትና አመስጋኝነትን ለመቀስቀስ ነበር። ዛሬ ሙዚቃ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለበት ሁኔታ ከጥንታዊ ባህልና አጠቃቀም ጋር ያለው ንፅፅር ምንኛ ይለያያል! የዝማሬ ስጦታን ለእግዚአብሔር ክብር ከመጠቀም ይልቅ ራሳቸውን ከፍ ከፍ ለማድረግ የሚያውሉት ስንቶች ናቸው! የሙዚቃ ፍቅር የማይጠነቀቁትን ሰዎች ደስታን በመፈለግ እግዚአብሔር እንዳይሄዱ ወደ ከለከላቸው ሰዎች በመሄድ ከዓለም ወዳጆች ጋር ህብረት እንዲፈጥሩ ይመራቸዋል። ስለዚህ በትክክል ጥቅም ላይ ቢውል ኖሮ ታላቅ በረከት የነበረው በተገቢው ሁኔታ ጥቅም ላይ ካለመዋሉ የተነሳ ሰይጣን አእምሮን ከተግባር ለማዘናጋትና ዘላለማዊ ነገሮችን እንዳያሰላስል ለማድረግ ከሚጠቀምባቸው እጅግ ውጤታማ ከሆኑ ዘዴዎች አንዱ ይሆናል። MYPAmh 190.1
ሙዚቃ በላይኛው አደባባይ የእግዚአብሔር አምልኮ አካል ነው። እኛም በውዳሴ መዝሙሮቻችን በተቻለን መጠን ወደ ሰማያዊ ኳየር ዝማሬ ውበት ለመድረስ መጣር አለብን። በትምህርት ውስጥ ድምፅን በደንብ ማሰልጠን አስፈላጊ ገፅታ ስለሆነ ችላ ሊባል አይገባም። Patriarchs & Prophets, P. 594. MYPAmh 190.2