መልዕክት ለወጣቶች

321/511

ሙዚቃ ውድ ሥጦታ

የመጽሐፍ ቅዱስ መዝሙሮች ታሪክ ስለ መዝሙርና ሙዚቃ ጥቅሞች ጠቃሚ በሆኑ አስተያየቶች የተሞላ ነው። ብዙ ጊዜ ሙዚቃ የክፉን አላማ ለማገልገል ታልሞ ጥቅም ላይ ውሏል። በመሆኑም እጅግ አታላይ ከሆኑት የፈተና መንገዶች አንዱ ሆኗል። ነገር ግን በትክክል ጥቅም ላይ ቢውል ኖሮ አስተሳሰብን ከፍ ወዳሉና ወደ ከበሩ ጉዳዮች ለማድረስ እና ነፍስን በእውነት ለመሙላትና ከፍ ለማድረግ ታቅዶ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ውድ ስጦታ ነው። MYPAmh 189.3

የእስራኤል ልጆች በምድረ በዳ በሚጓዙበት ጊዜ መንገዳቸውን በተቀደሰ የዝማሬ ሙዚቃ ደስታ እንደሞሉት ሁሉ እግዚአብሔር የዛሬንም ልጆች የመናኝ ጉዞ ሕይወታቸውን በዝማሬ ደስታ እንዲሞሉት ይጠይቃቸዋል። የእግዚአብሔር ቃላት በአእምሮ ውስጥ ተተክለው እንዲቀሩ ለማድረግ በመዝሙር ቃላቱን ከመደጋገም የበለጠ ውጤታማ የሆኑ ዘዴዎች እጅግ ጥቂት ናቸው። እንደዚህ አይነት መዝሙር አስደናቂ ኃይል አለው። ያልታረሙና ያልተስተካከሉ ተፈጥሮዎችን ጉልበት የማስገዛት ኃይል አለው፡ የተግባር መጣጣምን የማደፋፈርና ድፍረትን በማጥፋት ትጋትን የሚያዳክመውን ጨለምተኝነትን የማጥፋት ኃይል አለው። MYPAmh 189.4

ልብን በመንፈሳዊ እውነት ለመንካት እጅግ ውጤታማ ከሆኑ መንገዶች አንዱ ነው። ለተጨነቀችና ተስፋ ለመቁረጥ ለተቃረበች ነፍስ ለብዙ ጊዜ ተረስቶ የነበረው የህፃንነት ዘመን መዝሙር ከአእምሮ ትውስታ ብቅ በማለቱ ፈተናዎች ኃይል ያጡበትና ሕይወት አዲስ ትርጉምና አዲስ አላማ ይዞ የተነሳበትና ድፍረትና ደስታ ለሌሎች ነፍሳት ሊዳረስ የቻለበት ምን ያህል ጊዜ ነው! MYPAmh 189.5

መዝሙር እንደ ማስተማሪያ መንገድ ያለው ጠቀሜታም መረሳት የለበትም:: በቤት ውስጥ ጣፋጭና ንፁህ መዝሙሮች ይዘመሩ። ያን ጊዜ ጥቂት የቁጣ ቃላትና ብዙ ፈገግታ፣ ተስፋና ደስታ ይኖራል። በትምህርት ቤቶች መዝሙሮች ይዘመሩ:: ያን ጊዜ ተማሪዎች ወደ አምላካቸው፣ ወደ መምህሮቻቸውና ወደ እርስ በርሳቸው ይሳሳባሉ። MYPAmh 189.6

እንደ መንፈሳዊ አገልግሎት ክፍል በመሆን ዝማሬ ልክ እንደ ጸሎት ሁሉ የአምልኮ ተግባር ነው። MYPAmh 189.7

በርግጥ ብዙ መዝሙሮች ፀሎት ናቸው። ልጅ ይህንን እንዲያስተውል ቢማር ኖሮ የሚዘምራቸውን የመዝሙር ቃላት ትርጉም የበለጠ እያሰበ ለኃይላቸው ተገዥ ይሆን ነበር። አዳኛችን በእግዚአብሔር ክብር ወደሚያበራው ዘላለማዊ መሸጋሪያ ሲመራን ሳለ በዙፋኑ ዙሪያ ካለው ሰማያዊ ኳየር የውዳሴና የምስጋና ሃሳቦችን እንሰማለን። የመላእክት ዝማሬ የገደል ማሚቶ በምድራዊ ቤቶቻችን ሲያስተጋባ ልቦች ወደ ሰማያዊ መዘምራን ይጠጋሉ። የሰማይ ግንኙነት በምድር ላይ ይጀምራል። እዚሁ የውዳሴን ቁልፍ አሳብ እንማራለን። MYPAmh 189.8