መልዕክት ለወጣቶች
የአካል ልምዶች በአእምሮ ላይ ያላቸው ተጽእኖ
እዚህ የቀረበው ትምህርት በደንብ ልናስብበት የሚገባ ትምህርት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንድንፈጽም የሚነግረንን ነገሮች በጥብቅ መታዘዝ ለአካልም ሆነ ለአእምሮ በረከት ነው፡፡ የመንፈስ ፍሬ ፍቅር፣ ደስታና ሰላም ብቻ ሳይሆን መሻትን መግዛትም ነው፡፡ አካሎቻችን የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ስለሆኑ እንዳናረክሳቸው ታዘናል፡፡ MYPAmh 158.3
የዕብራውያን ምርኮኞች እንደኛው ስሜት የነበራቸው ነበሩ፡፡ ማታለል በሚችሉ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ቅንጦት መካከል ፀንተው ቆሙ፡፡ የዛሬ ወጣቶች በራስ ደስታ ማታለያዎች ተከበዋል፡፡ በተለይ በታላላቅ ከተማዎቻችን እያንዳንዱ ስሜትን ማርኪያ ዘዴዎች በቀላሉ የሚገኙና ማራኪ ሆነዋል፡፡ ልክ እንደ ዳንኤል ራሳቸውን እንዳያረክሱ እምቢ የሚሉ መሻታቸውን የመግዛት ሽልማት ያገኛሉ፡፡ በአካል ጥንካሬያቸውና ችግርን የመቋቋም ኃይላቸው መጨመር የተነሣ ለአስቸኳይ ጊዜ የሚሆን የተጠራቀመ የባንክ ክምችት አላቸው፡፡ MYPAmh 158.4
ትክክለኛ የሆኑ የአካል ልምዶች የአእምሮ የበላይነትን ያጎለብታሉ፡፡ የአእምሮ የእውቀት ኃይል፣ የአካል ጥንካሬና የምንኖረው የዕድሜያችን ዘመን በማይለወጡ ሕጎች መታዘዝ አለመታዘዛችን ላይ ይደገፋል፡፡ የተፈጥሮ አምላክ የተፈጥሮን ሕጎች በመጣስ በሚመጡ ነገሮች ላይ ጣልቃ አይገባም፡፡ ድልን ለማግኘት የሚታገል ሁሉ በነገር ሁሉ መሻቱን መግዛት አለበት፡፡ የዳንኤል የአእምሮ ጥረትና የዓላማ ጽናት፣ እውቀትን የመገብየትና ፈተናን የመቋቋም ኃይል ከጸሎት ሕይወቱ ጋር ተገናኝቶ በከፍተኛ ደረጃ ካልተወሳሰበ አመጋገቡ የተነሣ ነበር፡፡ MYPAmh 158.5