መልዕክት ለወጣቶች
መዳረሻችንን ማስተካከል
«እያንዳንዱ ሰው የወደፊት ሕይወቱ ንድፍ ሰሪ ነው፡፡» በሚለው አባባል ውስጥ ግሩም የሆነ ነገር አለው፡፡ ወላጆች ለልጆቻቸው የባሕርይ አሻራም ሆነ ለትምህርታቸውና ሥልጠናቸው ኃላፊነት ያላቸው ቢሆንም በዚህ ዓለም ላይ የሚኖረን ቦታና ጠቃሚነታችን በከፍተኛ ደረጃ የሚደገፈው በራሳችን በምንወስደው የተግባር አቅጣጫ ነው፡፡ MYPAmh 158.6
ዳንኤልና ጓደኞቹ በልጅነታቸው ጊዜ ትክክለኛ የሆነ ትምህርትና ሥልጠና አግኝተዋል፡፡ ነገር ግን ይህ ብቻ የሆኑትን እንዲሆኑ ሊያደርጋቸው አይችልም ነበር፡፡ ራሳቸው ለራሳቸው መወሰን የነበረባቸው ጊዜ ያውም የወደፊቱ ሁኔታቸው አሁን በሚከተሉት አቅጣጫ የሚወሰንበት ሰዓት መጣ፡፡ እነርሱም በሕፃንነታቸው ላገኙት ትምህርት ታማኝ ለመሆን ወሰኑ፡፡ የታላቅነታቸው መሠረቱ የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነበር፡፡ MYPAmh 159.1
የዳንኤልና የወጣት ጓደኞቹ ታሪክ በመንፈስ በተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተፃፈበት ምክንያት ቀጥሎ ባሉት ዘመናት ሁሉ ለሚኖሩ ወጣቶች ጥቅም ነው፡፡ እነርሱ መሻትን ለመግዛት ደንቦች ታማኝ መሆናቸውን በሚገልጽ ጽሁፍ አማካይነት ለዘመኑ ወጣቶች በክርስትና መሻትን መግዛት ላይ የተሰጠውን ብርሃን በመሰብሰብ ከጤና ሕጎች ጋር ትክክለኛ ግንኙነት እንዲፈጥሩ እየተነገራቸው ነው፡፡ MYPAmh 159.2