መልዕክት ለወጣቶች
ጤንነትን መስዋዕት በማድረግ የሚገኝ ትምህርት
አንዳንድ ተማሪዎች ሁለመናቸውን ለትምህርት አሳልፈው በመስጠት አእምሮዋቸው ትምህርት በማግኘት ላይ ብቻ ያተኩራል፡፡ አእምሮአቸው ይሰራል፣ ግን የአካል ኃይሎቻቸው ሥራ እንዲፈቱ ያደርጋሉ፡፡ ከዚህ የተነሣ አእምሮ ያለመጠን እየሰራ ሳለ ጡንቻዎች ምንም ሥራ ስለማይሰሩ ደካማ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ ተማሪዎች በሚመረቁበት ጊዜ ሕይወታቸውን መስዋዕት በማድረግ ትምህርታቸውን መማራቸው በግልጽ ይታወቃል፡፡ ጡንቻዎቻቸው በቂ እንቅስቃሴ ሳያገኙ አእምሮአቸውን በማስጨነቅ ለአመታት ቀንና ማታ ጥናታቸውን አጥንተዋል…፡፡ MYPAmh 157.1
ወጣቶች ሴቶች ብዙ ጊዜ ለተግባራዊ ሕይወት ከመጽሐፍት ጥናት ይልቅ የበለጠ ጠቃሚ የሆነውን የሥራ ዘርፍ ችላ በማለት በጥናት ላይ ያተኩራሉ፡፡ ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ለሕይወት ገጣሚዎች አይደሉም፡፡ ብዙ ጊዜ ከቤት ሳይወጡ በመቅራትና የሰማይን ንፁህ አየርና እግዚአብሔር የሰጠውን የፀሐይ ብርሃን ባለማግኘት ጤንነታቸውን ችላ ብለውታል፡፡ እነዚህ ወጣት ሴቶች ከትምህርታቸው ጋር የቤት ውስጥ ሥራንና ንጹህ በሆነ አየር ውስጥ እንቅስቃሴ ማድረግን አዋህደው ቢሆን ኖሮ ከትምህርት ቤት ሲወጡ ከሙሉ ጤንነት ጋር ይወጡ ነበር፡፡ MYPAmh 157.2
ጤና ታላቅ ሐብት ነው፡፡ ሟች ሰዎች ሊያገኙት የሚችሉት ትልቅ ሐብት ጤንነት ነው፡፡ ጤንነትን በመጉዳት ሃብት፣ ክብር ወይም እውቀት የሚገኝ ከሆነ እጅግ ውድ ዋጋ አስከፍሏል፡፡ ጤና ከጠፋ ከእነዚህ ስኬቶች አንዱም ቢሆን ደስታን ሊሰጥ አይችልም፡፡ Counsels to Teachrs, Parentes & Students, P. 285-286. MYPAmh 157.3