መልዕክት ለወጣቶች
ሚዛናዊ ትምህርት
በአካል እንቅስቃሴ ላይ የዋለ ጊዜ የባከነ አይደለም፡፡ ወጣ ብሎ ነፃ አየር ለመቀበል ጥቂት ጊዜ ብቻ በመስጠት ሁልጊዜ መጽሐፍትን በማጥናት ላይ የሚያተኩር ተማሪ ራሱን እየጎዳ ነው፡፡ እያንዳንዱን ሥራ በተሻለ ሁኔታ ለመሥራት ለእያንዳንዱ የአካል ክፍሎቻችን የተመጣጠነ እንቅስቃሴ አስፈላጊ ነው፡፡ ሌሎች የአካል ክፍሎች ሥራ ፈትተው አእምሮ ብቻ ያለመጠን በሥራ ሲጠመድ የአእምሮ ብርታት ማጣት ይከሰታል፡፡ የአካል ኃይሎች ጤናማ የአሰራር ቅኝታቸውን ያጣሉ፡፡ አእምሮ እውቀትን ለመጨበጥ ያለውን ዝግጁነትና ብርታቱን ያጣና ጤናማ ያልሆነ የአእምሮ መነሳሳት ይከተላል፡፡ MYPAmh 156.1
ወንዶችና ሴቶች ሚዛናዊ የሆነ አእምሮ እንዲኖራቸው ከተፈለገ የአካል ኃይሎች በሙሉ ጥቅም ላይ መዋልና ማደግ አለባቸው፡፡ ዛሬ በዓለም ላይ አንዱ የአካል ኃይላቸው ብቻ አድጎ ሌሎች ክፍሎች ግን ሥራ በመፍታታቸው ምክንያት ድንክየ የሆኑባቸው ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ የብዙ ወጣቶች ትምህርት ውጤታማ ያልሆነ ነው፡፡ ለተግባራዊ ሕይወት የሚያስፈልገውን ሥራ ችላ በማለት ያለ መጠን የቀለም ትምህርትን ያጠናሉ፤ የአእምሮ ሚዛንን ለመጠበቅና ሁሉም የአካል ክፍሎች የተመጣጠነ እድገት እንዲኖራቸው ለማድረግ የተመጣጠነ የአካል እንቅስቃሴ ከአእምሮ ሥራ ጋር መቀላቀል አለበት፡፡ Counsels to Teachers, Parents and Students, P.295-296. MYPAmh 156.2