የወንጌል አገልጋዮች
የቤተ ክርስቲያንን ዕረዳቶች ማሠልጠን
ንግግሩን፤ ሥራውን፣ ጸሎቱን ሁሉ ራሴ ማካሄድ አለብኝ ብሎ ወንጌላዊው ማሰብ የለበትም፡፡ በየቤተክርስቲያነ እረዳቶችን ያሠልጥን፡ አገልግሉት በመምራት፣ መጽሐፍ ቅዱስ በማንበብ ልዩ ልዩ ሰዎች ቤተ- ክርስቲያንን ያገልግሉ፡፡ ይህን ሲያደርጉ የራሳቸውን ሥጦታ ከማዳበራቸውም በላይ ቀስ በቀስ ቤተ-ክርስቲያንን ለማገልገል ይሠለጥናሉ፡፡ GWAmh 122.5
«አንዳንድ ቄሶች የሠራተኛች አለቃ ወይም የመርከብ አዛዥ ይመስላሉ፡፡ የተሾሙባቸው ሰዎች የተሰጣቸውን ግዳጅ በደንብ ማከናወን አለማከናወናቸውን ይቆጣጠራሉ፡፡ ወደ ዝርዝር ጉዳይ የሚገቡት አንዳንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ GWAmh 123.1
«የአንድ ፋብሪካ ባለንብረት የሾመው ሰውየ የተበላሸውን መሣሪያ ሲጠግን ግማሽ ደርዘን ተራ ሠራተኞች ቆመው ሲመለከቱት : ባለንብረቱ የነገሩን መጥፎነት ተመለከተና ኃላፊውን ወዲያው ሙሉ ደሞዝ ሰጥቶ አሰናበተው፡፡፡ ያ ኃላፊ ነገሩ አንዲገለጽለት ዝርዝር ማስረጃ ጠየቀ፡፡ ባለንብረቱ እንዲህ ሲል አስረዳው:- «6 ሰዎች እንድታሠራ ቀጠርሁህ፤ ስድስቱ ተቀምጠው አንተ የአንድ ሰው ሥራ ብቻ ስትሠራ አንተ የሠራኸውን ሥራ ከስድስቱ አንዱ ሊሠራው ይችላል፡፡ አንተ ስድስቱን ስንፍና እንድታስተምርልኝ የሰባት ሰዎች ደሞዝ ልከፍልህ አልችልም” አለው፡፡ GWAmh 123.2
«ይህ አጋጣሚ በአንዳንድ ጊዜ ሲሠራበት ሲችል በሌላ ጊዜ ግን አያዋጣም፡፡ አንዳንድ ወንጌላዊያን መላው የቤተ-ክርስቲያን አባሎች በሥራው አንዲካፈሉ ማስተባበር አይችሉም:: ቀሳውስት የቤተ- ክርስቲያንን አባሉች ኃይል ከሥራ ላይ ሊያውሉት ቢችሉ ኖር የበለጠ ውጤት ያገኙ ነበር፡፡ የበለጠ የጥናት ገቢ አትርፈው እውቀታቸውን ከማዳበራቸው በላይ ለአንዳንድ አለመግባባትም ቦታ አይኖረውም ነበር፡፡ GWAmh 123.3
አንዳንድ ሰዎች በሥራቸው ይሳሳታሉ፤ ነገር ግን ስህተታቸውን እንዴት አንደሚያርሙ በትህትና ሊገለጥላቸው ይገባል፡፡ ስለዚህ ሠራተኞች ላነሱት ለእግዚአብሔር ሥራ ብዙ ዕረዳቶችን ሊያሰለጥን ይችላል፡፡ ኃላፊነትን የሚሸከሙ ሰዎች ያስፈልጉናል፡፡ እንደነዚህ ያሉት ሰዎች የሚገኙት በሥራው ላይ ከልባቸው ሲሰለፉበት ነው፡፡ GWAmh 123.4