የወንጌል አገልጋዮች
የሥራ ክፍፍል
በቤተክርስቲያን ውስጥ ለዕድገት አንቅፋት የሆኑ ምክንያቶች አይታጡም፡፡ ላላመኑ ቃለ-እግዚአብሔርን በምናስተላልፍበት ጊዜ የቤተ-ክርስቲያን አባሎች ሥራውን ለወንጌላዊያን ብቻ በመተው ቆመው ተመልካቾች ይሆናሉ፡፡ እነርሱ ኃላፊነት አንዳለባቸው አይሰማቸውም፡፡ በዚህ ምክንያት የመልካም ወንጌላዊያን ጥረት ውጤቱ ሳያምር ይቀራል፡፡ ጥሩ ስብከት ቢሰበክም፤ ሕዝቡ የተፈለገውን መልዕክት ቢያዳምጡም ወንጌላዊው ለክርስቶስ የሚያስረክበው ነዶ ሳይሰበሰብ ይቀራል፡፡ GWAmh 122.2
ወንጌላዊው አማኞች ባሉበት አካባቢ ሲሠራ ላላመኑት ከማስተማሩ በፊት ያመኑትን ከሥራው ጋር ተባባሪ እንዲሆኑ ማነቃቃት: ለየግላቸው በመናገር ያመኑትን ለሌሎች የማካፈል ልምድ እንዲኖራቸው ያስገንዝባቸው፡፡ በጸሎታቸውና በሥራቸው ሲደግፉት ያን ጊዜ ይሳካለታል፡፡ GWAmh 122.3
ዘላቂ ሥራ ሊሠራ የሚችል እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን አባል ኃላፊነት ሲሰማው ነው፡፡ እያንዳንዱ አባል ለሥራው ዕድገት የሚሠራው የራሱ መኖሩን : ያለጥረትና ያለድካም ሰዎችን ማዳን አይቻልም፡፡ ወንጌላዊው ሰዎችን ሊያድን አይችልም፡፡ እርሱ የክርስቶስ ብርሃን የሚያልፈበት ቱቦ ነው፡፡ ሰዎች ብርሃኑን ከተመለከቱ በኋላ እነርሱ በፈንታቸው ለሌሎች ማስተላለፍ አለባቸው፡፡ GWAmh 122.4