የወንጌል አገልጋዮች
ለሌሎች የምታደርገው ጥረት ያድንሃል
ትጉ ቤተ ክርስቲያን ፅድገቱ አያቋርጥም፡፡ አባሎቹ ሌሎችን የመርዳት ፋላጎተ ያድርባቸዋል፡፡ በአንድ የክረምት ቀን በበረዷማ ቦታ ሲጓዝ አካሉ በሙሉ በብርድ ስለደነዘዘበት ሰው አንብቤአለሁ፡፡ በብርዱ ምክንያት ስቃይ ተሰምቶት መሞቴ ነው ብሎ ሲያቃስት እንደርሱ በብርድ የተኮማተረ ሰው ድምፅ ሰማ፡፡ ለሰውየው አዘነለትና ሊያድነው ወሰነ፡፡ በሰውየው ላይ የተቆለለውን የበረዶ ክምር አስለቅቆ ሰውየውን አስነሳው:፡ ሰውየው መራመድ ስለቻለ ብቻውን አንኳን ለመሄድ አልችልም ብሎ ባሰበው አስቸጋሪ ቦታ ደግፎ አሳለፈው፡፡ GWAmh 124.1
ያን ሰው ከደህና ቦታ ካሳለፈው በኋላ ሲያስብ ሰውየውን በማዳኑ ራሱንም እንዳዳነ ተሰማው፡፡ ሰውየውን ለማትረፍ ባደረገው ጥረት አካሉ በቂ ሙቀት ስላገኘ ብርዱን ሊከላከል ቻለ፡፡ GWAmh 124.2
ሌሎችን በመርዳት የራሳቸው ክርስትና እንደሚያድግና አንደሚበረታ ለወጣት አማኞች ሲገለጥላቸው ይገባል፡፡ ወደዘለዓለም ሕይዎት የሚያደርሰው መንገድ አስቸጋሪ ነው ብለው የሚያስቡ ሌሎችን በመርዳት ይሞክሩት፡፡ ከጸሎት ጋር የተባበረ እንዲህ ዓይነት ጥረት የእግዚአብሔርን ፀጋ ያስገነዝባል። መንፈሣዊ ዕድገት መለኮታዊው ኃይል ይታይበታል፡፡ የክርስትና ሕይወቱም እውነተኛ፣ ጸሉተኛ፣ ቁምነገረኛ ይሆናል፡፡ GWAmh 124.3
ሰማያዊ ነገር የምንፈልግ ሁሉ የዚህች ዓለም አንግዶችና መፃተኞች መሆናችን አለመርሣት ዋና ነገር ነው፡፡ ለጌታ ለመሥራት ቃል ኪዳን የገቡ ሰዎች ነፍሳትን መመለስ አላማቸው ሊሆን ይገባል፡፡ የቤተ- ክርስቲያን አባሎች ሳምንቱን በሙሉ በታማኝነት ሲሠሩ ሰንብተው በሰንበት ቀን ሲመጡ ያከናወኑትን : ስብሰባው ሁሉንም የሚያበረታታ፣ ሲያምር እንደተገኘ ምግብ ሊሆን : ክርስቲያኖች ነፍሳትን ለመመለስ ያላቸው ፍላጎት የክርስቶስን ምሣሌነት የተከተለ የሆነ አንደሆነ የተሰጡትን ተስፋ ለመፈጸም አዲስ ኃይል ይቀበላሉ፡፡ ሌሎችን በመርዳት ያገኙትን ጥቅም ለሌሎች በመናገር ደስታ ያገኛሉ፡፡ GWAmh 124.4