የወንጌል አገልጋዮች

72/217

በጠባይህና በአለባበስህ መጠንቀቅ

ወንጌላዊያን ውጤት አናገኛለን ብለው በመድረክ ላይ አንደ ቲያትር ተዋንያን መሥራት አይፈቀድላቸውም፡፡ ተዋንያን ሳይሆኑ የእውነት መምህራን ናቸው፡፡ ክብር የጐደለው አጉል መወራጨት ለተነገረው እውነት ኃይል አይጨምርለትም፡፡ ይልቅ ቅን አስተያየት ያላቸውን ክርስቲያናት ያሳዝናል፡፡ GWAmh 107.4

ሕይወቱን ለክርስቶስ ያስገዛ ወንጌላዊ ምን ጊዜም የእግዚአብሔር መልዕክትኛ መሆኑን አይረሳም፡፡ ምን ጊዜም የእግዚአብሔር መሪነት እንደማይለየው ያምናል፡-፡ በራሱ መመካት፣ በተማረው ትምህርት መታበይ ሲያልፍም አይነካካው፡፡ ጠቅላላ ዓላማው ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ መመለስና በማስረጃና በሕይወቱ አርአያነት ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር በግ ማመላከት ነው:: ከእግዚአብሔር ኃይልና ሥልጣን እንደተቀበለ በማወቅ ያስተምራል፡፡ ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ ሊያስጠጋ በሚችል አይነት አነቃቂነት ማስተማር አለበት፡፡ GWAmh 107.5

በአለባበስ መጠንቀቅ ተፈላጊ ነገር ነው:: ማዕረጉን በክብር የሚያጎናጽፍለትን የመንፈስ ልብስ መልበስ አለበት፡፡ በዚህ ሁኔታ ብዙ ወንጌላዊያን ይሳሳታሉ፡፡ አለባበሳቸው ሥርዓት የጐደለውና ንጽህና የሌለበት ነው፡፡ ዓለምን የፈጠረና የሚጠብቅ የሰማይ አምላክ በሰራተኞቹ ይከበራል ወይም ይዋረዳል፡፡ ስለ ቤተ መቅደሱ አገልግሎት እግዚአብሔር ለሙሴ ዝርዝር መመሪያ ሰጠወ፡፡ «የተቀደሰውን ልብስ ለክብርና ለጌጥ እንዲሆን ለወንድምህ ለአሮን ሥራለት፡፡› (ዘፀዓት 28:2) GWAmh 107.6

የካህኑ የኑሮ - አመራርና አለባበስ የእግዚአብሔርን ቅዱስነት የሚያሳስበው መሆን አለበት፡፡ የአምልኮቱን ብፅዕናና በፊቱ የሚቀርቡት ንጹህ ሊሆኑ እንደሚገባቸው ያስተውላል፡፡ GWAmh 108.1

በጫማቸው ያለው አቧራ ቤተመቅደሱን አንዳያረክሰው ካህናቱ ሲገቡ ጫማቸውን በአደባባዩ አውልቀው ከገቡ በኋላ በመሠዊያው ከማገልገላቸው በፊት አጆቻቸውን መታጠብ. ነበረባቸው፡፡ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ ሰዎች ሁሉ ጉድለታቸውን ማስወገድ አንዳለባቸው የሚያስገነዝብ ትምህርት በየቀኑ ይሰጥ ነበር፡፡ GWAmh 108.2

በአለባበሱ ጉድለት ያለበት ወንጌላዊ፣ እግዚአብሔርን ከማሳዘኑም በላይ ለሥራው ያለውን ዝቅተኛ ግምት ለሰዎች ያሳያል፡፡ የልብስ ንጽህናን ተፈላጊነት በማሳየት ፋንታ ለሌሎች የግዴለሽነት መንገድ ይከፍታል፡፡ GWAmh 108.3

እግዚአብሔር ወንጌላዊያን በአለባበሳቸውና በጠባያቸው ለሥራው ገጣሚ መሆናቸውንና የሥራቸውን ከፍተኛነት አንዲገልጡ ይፈልጋል፡፡ ሰዎች መንፈሳዊ ደረጃቸውን ከፍ ለማድረግ ይችሉ ዘንድ ምሣሌ ይሁነአቸው፡፡ GWAmh 108.4

ሰዎች የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ለማጥፋት ይችላሉ! የምርጫ መብት ተሠጥቷቸዋል፡፡ የፈለጉትን ሊሠሩም ነፃነት አላቸው፡፡ እግዚአብሔርን ሊታዘዙ ወይም ላይታዘዙ ይችላሉ፡፡ ግን ውጤቱን አይዘንጉ፡፡ GWAmh 108.5

የዘለዓለም ዕውነትን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል እያንዳንዱ ሰው ኃላፊነት አለበት፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ምን ጊዜም ቢሆን መጐትጐቱን አቋርጦ አያውቅም፤ መቀበል አለመቀበል በሰዎች ይወሰናል፡፡ በክርስቶስ ፈንታ አሱን ወክለው የሚሠሩ ሰዎች ሥራ የማያጸጽት ቢሆን እንዴት መልካም ነው! GWAmh 108.6