የወንጌል አገልጋዮች
የጉባዔ ጸሎት
በጉባዔ የሚጸለይ ጸሎት አጭርና ግልጽ መሆን አለበት፡፡ በረዥም ድግግም የስብስባን ጊዜ አሰልች አንድናደርግ እግዚአብሔር አይፈልግም፡፡ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን አድካሚ፣ ረዥም ጸሎት አንዲጸልዩ አላስተማራቸውም፡፡ «ስትጸልዩም እንደግብዞች አትሁኑ፡፡ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና ዕውነት አላችኋለሁ ዋጋቸውን ተቀበሉ፡፡ ፈሪሣዊያን የጸሎት ጊዜ ይወስኑና ጊዜው ሲደርስ በሰው ፊት ቆመው በጩኸት ይጸልዩ ነበር፡፡ እንዲህ ያለን የታይታ ጸሎት የሱስ በጥብቅ ነቅፎታል፡፡ ግን የጉባዔ ጸሎት ይቅር አላለም፡፡ እርሱ ራሱ ከደቀመዛሙርቱና ከሕዝብ ጋር ይጸልይ ነበር፡፡ ደቀመዛሙርቱን የጉባዔ ጸሎት አጭር መሆን አንዳለበት አስጠናቸው፡፡ GWAmh 109.1
ነገር ግን አንደ ያዕቆብ በረከት ሽቶ የሚታገል ነፍስ በግል ረዥም ጸሎት ያድርግ:: እግዚአብሔርን ከመለመን ይልቅ ለእርሱ ሰፋ ያለ ተራ ንግግር እንደማሰማት የሚቆጠር አሰልች ጸሎት አሰ : GWAmh 109.2
እንዲህ ያለ ጸሎት የሚጸልዩ ሰዎች ክርስቶስ ለደቀመዛሙሙርቱ ያስተማረውን ጸሎት ቢማሩ መልካም ነው:: ረዥም ጸሎት ሰሚዎችን ያሰለቻል እንጂ ለሚሰጠው ተከታይ መልዕክት አያዘጋጃቸውም፡፡ GWAmh 109.3
የግል ጸሎት ችላ በመባሉ በጉባዔ ረዥም ጸሎት ይዘወተራል፡፡ ሳምንቱን ሙሉ የረሱትን ተግባር ወንጌላዊያን በአንድ ቀን ለማከናወን አይሞክሩ፡፡ የዚህ ዓይነት ጸሎት የብዙዎችን መንፈሣዊ ዕድገት ዝቅ ያደርግባቸዋል፡፡ GWAmh 109.4
ወንጌላዊ ማስተማር ሳይጀምር በፊት የአምላክን የቅርብ ዕርዳታ መጠየቅ አለበት፡፡ የተጠማች ነፍሱን ወደ ፈጣሪ አቅርቦ ከፀጋ ጠል ያርካ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ስለሚነካ ጉባዔውን ከየሱስ ጋር ሳያገናኝ አያሰናብተውም፡፡ እነዚህን አዳማጮቹን ሁለተኛ እአንደማያገኛቸው በማሰብ የልብ ተማዕጽኖ ያቀርብላቸዋል፡፡ የሰዎችን ልብ የሚመረምር አምላክ ትክክለኛውን መልዕክት አንዲናገር ኃይል ይሠጠዋል፡፡ GWAmh 109.5