የወንጌል አገልጋዮች

71/217

ጠቃሚ አስተያየቶች

ንግግር:- - አንዳንድ ወንጌላዊያን ሰእግዚአብሔር የሚናገሩትን አንዲያቀብላቸው ሳይፈቅዱለት፤ የሚናገሩትን በሙሉ ዘርዝረው ጽፈው ይይዛሉ፡፡ እያንዳንዱ የሚናገሩት ቃል ስለታቀደ ከዚያ ውጭ ለመናገር አይከጅሉም፡፡ ይህ አደገኛ ስህተት ነው፡ ካልታረመ በቀር የወንጌላዊውን አስተሳሰብ ያጠብበታል፡፡ መንፈሳዊ ሕይወትና ኃይል ይለየዋል፡፡ GWAmh 103.1

ወንጌላዊ የጻፈውን አጥንቶ የሰጠው ትምህርት የተነበበ ድርሰት ከሚያስገኘው ውጤት አይሻልም፡፡ በቃል የተጠና ስብከት አምብዛም የመንፈስ ኃይል የለበትም፡፡ ጌታ ሆይ ለሕዝብህ ምን ልናገር? ብለው ከጠየቁ በኋላ ጌታ የሚናገራቸውን ማዳመጥ አለባቸው፡ እግዚአብሔር ወንጌላዊያኑን አንዲተማመኑበት ይፈልጋል፡፡ ከሰማይ የተላከ መልዕክት ተቀብለው ለሕዝቡ ለማስተላለፍ አንዲችሉ ልባቸውን ለአምላክ አስረክበው አስተሳሰባቸውን አንዲመራው መፍቀድ አለባቸው፡፡ ለተሰበሰቡት ሰዎች የሚጠቀም መልዕክት መንፈስ ቅዱስ ያቀብላቸዋል፡፡ GWAmh 103.2

አክብሮት፡- የክርስቶስን የሕይወት ታሪክ እንደ አንድ ተራ የታሪክ ሰው በመቁጠር በአልባሌ ቦታ የሚወያዩበት ወንጌላዊያንን አይቻለሁ፡፡ እርግጥ ወንጌላዊያን ክርስቶስ እንደ ሰው ሆኖ አንደነበር ለ.ናገሩ ይችላሉ፡፡ GWAmh 103.3

ይህ ቅዱስ ስም እንዲህ ያለጥንቃቄ ሲነሳ መስማት ልገልጽ ከምችለው በላይ ያሳዝነኛል፡፡ ምክንያቱም ምንም አንኳን እነዚህ ሰዎች መምህራን ቢሆኑም ስለክርስቶስ በቂ ዕውቀት እንዳልገበዩ፣ ከእርሱ ጋር በሚገባ አንዳልተዋወቁ ስለሚነግረን ነው፡፡ የክርስቶስን ሕይወት ክፍተኛ ግምት እንዲሰጡት የሚረዳቸው በቂ ዕውቀት የላቸውም፡፡ GWAmh 103.4

የክርስቶስን ጠባይ በደንብ የተገነዘቡ ሰዎች ራሴ እበቃሰሁ የሚል ስሜት ወይም የዕቡይነት ባሕርይ አይታይባቸውም፡፡ የራሳቸውን ጉድለት ከክርስቶስ ሙሉነት ጋር በማመዛዘን ትህትና ያድርባቸዋል፡፡ ዕምነታችቸውን በክርስቶስ ኃይል ላይ ያሳርፉታል፡፡ በየቀኑ ከክርስቶስ ጋር መራመድ አምነትን ያጐለምሳል፡፡ መንፈሳዊን ዕድገት ያፋጥናል፤ እርሱን ለመምሰል ምኛትን ያሳድራል፣ የሚያበረታ ኃይል ለማግኘት ጸሎትን ያስዘወትራል፡፡ GWAmh 104.1

የማይስማማ ማብራሪያ:- ወንጌላዊያን ስብከታቸው የማይገጥም ማብራሪያ ማዋል የለባቸውም፣ ከተናገሩት እውነት ሰዎችን ያርቃሉ፡፡ የሚያስቅ ወይም አስተሳሰብን የሚያዝናና ታሪክ እአንደማስረጃነት ማቅረብ በጥብቅ ክልክል ነው፡፡ የወንጌል መልዕክት በቁም ነገር በተሞሉ ቃላት መቅረብ አለበት፣ የሚሰጠው ማስረጃም ገጣሚ መሆን አለበት፡፡ GWAmh 104.2

መስልቸትን መቆጣጠር፡፡- አንድ ወንጌላዊ በጠባብ ክፍል የሚሰብክ ከሆነ ሰዎቹ ይዝላሉ፡፡ የሞቀው አየር ያደክማቸውና አእምሮአቸው ይደነዝዛል፡፡ ወንጌላዊው የአስተማሪነት ዘዴ መጠቀም አለበት፡፡ አንዲሁ በመናገር ፋንታ በጥያቄና መልስ ያስተምር፡፡ ያን ጊዜ አእምሮአቸወ› ይነቃል፡፡ የሚነገረውን ንግግር ሊያስተውሉ ይችላሉ፡፡ GWAmh 104.3

አነስተኛ ስብሰባ:- በአንድ ስብሰባ የተገኙት ሰዎች በቁጥር አነሱ ብሎ ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም፡፡ ሁለት ወይም ሶስት ብቻ ቢሆኑም ከመካከላቸው የመንፈስ ትግል አንዳለባቸው ማን ያውቃል? ለአንድ ነፍስም ቢሆን እግዚአብሔር መልዕክት ያቀብላል፡፡ በእርሱ አማካኝነት ሌሎች ወደ ዕውነት ይሳቡ ይሆናል፡፡ ለአንተ ባይታወቅህም የሥራህ ውጤት በሺህ እጅ ይባዛ ይሆናል፡፡ GWAmh 104.4

ባዶዎቹን መቀመጫዎች በመመልከት ተስፋ አትቁረጥ:: እግዚአብሔር መልዕክቱን ለዓለም ለማዳረስ የሚያደርገውን ተመልከት፡፡ ከመለኮት ዕርዳታ ጋር መተባበርህን አትዘንጋ፡፡ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች አንደሚያዳምጡ አድርገህ ከልብህ በእምነት ተናገር፡፡ GWAmh 104.5

አንድ ወንጌላዊ በአንድ የክረምት ወር ለመስበክ ወደ ቤተክርስቲያን በጧት ሄደ፡፡ አንድ ሰው ብቻ አገኘ: በሙሉ ስሜት ሰበከለት፡፡ ይህ ሰው ተመለሰና ሚሲዮናዊ ሆኖ ብዙ ነፍሳትን መለሰ፡፡ GWAmh 104.6

አጭር ስብሰባ:- በእንዲህ ያለ ጊዜ የሚሰጠው ትምህርት በአጭሩ ዋና ዋና ፍሬውን የሚያስረዳ መሆን አለበት፡፡ ረዥም ስብከት ተናጋሪውን ከማድከሙ በላይ ሰሚዎቹንም ያሰለቻል፡፡ ተናጋሪው ተፈላጊ መልዕክት ያለው ቢመስለውም እርሱም ከመጠን በላይ አንዳይደክም፣ አዳማጮቹንም ከሚያስታውሱት በላይ አንዳይጭናቸው መጠንቀቅ አለበት፡፡ GWAmh 105.1

አንድ ጊዜ የተናገራችሁትን ሁሉንም ትምህርት ሰሚዎቹ የሚይዙላችሁ አንዳይመስላችሁ፡፡ ከአንድ ፍሬ ነገር ወደሌላው በፍጥነት መዛወር አደገኛ ነው:: አጫጭር ትምህርት ግልጽ ሆኖ በተደጋጋሚ መሰጠት አለበት:: ከረጅም ስብከት ይልቅ አጫጭር ትምህርቶች የማስተዋል ሁኔታ አላቸው፡፡ ወንጌላዊያን የሚያስተምሩትን ትምህርት ሰምተው የማያውቁ ሰዎች መኖራቸውን ባለመዘንጋት ደጋግመው መናገር አለባቸው፡፡ GWAmh 105.2

ቀጥተኛነት፡- ብዙ ተናጋሪዎች ይቅርታ በመጠየቅና የመግቢያ ንግግር በማራዘም ጊዜ ያጠፋሉ፡፡ አንዳንዶቹማ ይቅርታ ሲጠይቁ አንድ ግማሽ ሰዓት ገደማ ያሳልፋሉ፡፡ ጊዜ በመባከኑም ምክንያት ዋናውን ትምህርት በሚያካሂዱበት ጊዜ አደማጮችን ያስለቻሉ፡፡ ይቅርታ በመጠየቅ ጊዜ ከማባከን ይልቅ የሚተላለፈው መልዕክት ከእግዚአብሔር የተሰጠ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል፡፡ የሚነገረውን ትምህርት ግልጽ አድርጐ ማቅረብ ተገቢ ነው:: ማብራሪያ ለማያስፈልጋቸው ግልጽ ለሆኑ ነገሮች ብዙ ጊዜ ይጠፋል፡፡ ነገር ግን ተፈላጊዎቹ ፍሬ ነገሮች ግልጽ በሆነ ቋንቋ መናገር አለባቸው፡፡ GWAmh 105.3

ተመስጦ:፡- አንዳንዶች በአንድ ሀሳብ ላይ ከመጠን በላይ ይመሰጣሉ፡፡ ሌላ ሀሳቦችን ሁሉ ዘንግቶ በተለየ ሀሳብ ላይ መመሠጥ አደገኛ ነው፡፡ በንግግር ልውውጥ ጊዜ ችክ ያለና አዳማጩን የሚያሰለች ነው::: ሲጽፉም ዘና ያለ ጽሑፍ አይጽፉም፡፡ ለሕዝብ ሲናገሩ ሙሉ ሀሳባቸው በዚያው በንግግሩ ላይ ስለሆነ ከመጠን በላይ ጥልቅ ንግግር ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ይህን ዓይነት ንግግር ብዙዎቹ ላይከተሉት ይችላሉ፡፡ የእውነተ ዘር ከመቀበሩ የተነሳ ያለመብቀል ዕድል ያጋጥመው ይሆናል፡፡ GWAmh 105.4

ግልጽነት፦ ክርክር የሚያስፈልግበት ጊዜ ይኖራል፤ ለእግዚአብሔር ሥራ የበለጠ አገልጋይነት ያለው ግን ግልጽ መግለጫ ነው፡፡ ክርስቶስ ሲያስተምር ማንም መሐይም እንደሚያስተውለው አድርጐ ነበር፡፡ በንግግሩ በከባድ ቃላት፣ በረዥም ዓረፍተ ነገር አዳማጮቹን አላስቸገረም፡፡ ተራ ሕዝብ በሚያስተውለው ቀላል ቋንቋ አስተማረ፡፡ ሰዎች ከሚያስተውሉት በላይ ጥልቅ አገላለጽ አላደረገም፡፡ GWAmh 105.5

ወንጌላዊያን ሲያስተምሩ ግልጽና ቀላል ዘዴ ይኑራቸው፡፡ ከአደማሙቹ አብዛኛዎቹ ግልጽ ማስረጃ የሚሹ መሆናቸውን አይዘንጉ፡፡ ሕዝቡ በወንጌል ዕውቀቱ በኩል ከሚገባው (ከሚገመተው) በታች ነው:: GWAmh 106.1

ከኮሌጅ ምሩቃን፣ ከታላላቅ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከግሩም ተናጋሪዎች መካከል አብዛኛዎቹ ጥቃቅን ነገሮችን ሲከታተሉ ተፈላጊውን ነገር ችላ ብለውታል፡፡ GWAmh 106.2

ተናጋሪው ለእንደዚህ ዓይነት ሰዎች ሲያስተምር አብዛኛውን ጊዜ ለተማሩ ሰዎች አንደሚናገር ስለሚሰማው ከባድ ትምህርት ይሠጣቸዋል፡፡ ኃጢዓት በቀላሉ ሕግን መተላለፍ መሆኑን አያስረዳቸውም፡፡ የመዳንን ዕቅድ አያብራራላቸውም፡፡ የሰዎቹን ልብ የሚነካው ክርስቶስ ስለ እነርሱ እንደሞተላቸው ሲያውቁ ነበር፡፡ GWAmh 106.3

መነቃቃት:- አምላክ ሰዎችን እንደ መሣሪያው አድርጐ ባለ ኃይላቸው ሲጠቀምባቸው የሰይጣን ልጆች «ተመጻዳቂዎች» ይሏቸዋል፡፡ ሕዝቡን ማስጠንቀቅ መመጻደቅ አይደለም፡፡ ነቃፊዎች ይጠንቀቁ፤ ትርፉ ተዝብት ነው አንጂ እውነተኛነት በነቀፋ ምክንያት አይታጠፍም፡፡ ለይምሰል የሚሆኑ መነቃቃቶች ቢኖሩም ሁሉም መነቃቃቶች በጥርጥር መልክ መታየት የለባቸውም፡፡ አንደ ፈሪሣዊያን «ይህ ሰው ኃጥዓንን ይቀበላል” ሉቃስ 15፡2. ማለት የለብንም፡፡ በክርስቶስ ሕይወት ውስጥ በሥራው አንዳናሾፍ የሚያስተምሩን ብዙ ማስረጃዎች አሉ:: የእግዚአብሔር ፀጋ ኃጥዓንን ሲያድስ መልአክት ይደሰታሉ፡፡ ነገር ግን ይህ ታላቅ ሥራ በማያምኑ ዘንድ አንደ መመጻደቅ ተቆጥሯል፡፡ እግዚአብሔር የላከው መልዕክትኛም እንደ ደንቆሮ ይቆጠራል፡፡ GWAmh 106.4

የሰንበት አገልግሎት፡- የሰንበትን አገልግሎት አንዲመራ የተዘጋጀ ሰው በእግዚአብሔር ቃል አማካኝነት ሕዝቡን ለማስደስት መጣር አለበት:: ስለ ክርስቶስ ለማሰብ ጊዜ እስኪያጡ ድረስ አዳማጮቹን በንግግር ብዛት ማድከም የለበትም፡፡ GWAmh 106.5

አድማጮቹ ለእግዚአብሔር ምሥጋና ለማቅረብ ጊዜ እንዲያገኙ አገልግሎቱ አጭር መሆን አለበት:: የምሥጋና ሥጦታዎች የእግዚአብሔርን ስም ያከብሩታል፡፡ በቅዱሳን ስብሰባ ሁሉ መልአክት እግዚአብሔር በመዝሙር፤ በጸሎትና በምስጋና ሲወደስ መስማት ደስ ይላቸዋል፡፡ GWAmh 107.1

የጸሎት ስብሰባ ዕርዳታንና መበረታታትን ማስገኘት አለበት፡፡ ሁሉም በተካፋይነት ባለመብት መሆኑን መገንዘብ: በህብረት ስብሰባ ሁሉም ተካፋይ፣ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አይዘንጋ:: የሚሰጡት ምስክርነቶች አጭርና ለሌሎች ትምህርት የሚሰጡ መሆን አለባቸው፡፡ GWAmh 107.2

አንድ ሰው ሃያ ወይም ሠላሣ ደቂቃ ቢቆይ ያስለቻል፡፡ ይህ የስብስባውን መንፈስ ያጠፋዋል፡፡ GWAmh 107.3