የወንጌል አገልጋዮች
ለአንድ ወንጌላዊ የተሰጠ ምክር
የተወደድህ ወንድሜ፣ .. ይህ መልዕክት ከአምላካችን ዘንድ በእኔ በኩል ተልኮልሃል፡፡ በንግግር ቸር በተግባርህም ጨዋ ሁን፡፡ በንግግርህ ግዴለሽ፤ በአስተዳደርህ ጨቋኝ መሆን ጀምረሃልና ተጠንቀቅ፡፡ ጌታችን ወደ ፈተና እንዳትገባ ተግተህ ጸልይ : የብስጭት አነጋገር ጌታን ያስቆጣል፣ መጥፎ ቃላቶችም ጉዳት ያስከትላሉ፡፡ በንግግርህ እንድትታረም፤ ተጠንቅቀህ አንድትናገር፤ በአነጋገር ዘዴህ ወይም በአጠራርህ የቁጣ ምልክት አንዳይታይብህ አስጠነቅቅህ ዘንድ ታዝዣለሁ፡፡ በምትናገረውና በምትሠራው የክርስቶስ ተከታታይነትህ ይታወቅ፡፡ ያልተለወጠ የተፈጥሮ ጠባይህ ሥራህን አያበላሽብህ፡፡ የተፈተኑትን መርዳትና ማበርታት : የራስህን ስሜት ባልተገቡ ቃላት : አንተ ለምትሠራላቸው፤ ለመንጋው ሁሉ ክርስቶስ ሕይወቱን ይለውጣል፡፡ ከአፍህ የሚወጣ ቃል ነፍሳትን ወደ ስህተት መንገድ መምራት የሰበትም፡፡ የወንጌላዊ ጠባይ የክርስቶስን አራአያነት መከተል አለበት፡፡ GWAmh 101.3
ቁጡና ትዕግሥት የጐደለው አነጋገር ለእግዚአብሔር ሥራ እንቅፋት ነው:: የዕለት ኑሮህ በክርስቶስ የተመራ ከሆነ ጤናማና ስምም የሆነ ጠባይ ይታይብህአል፡፡ ውክልናህን አሳምር፣ ከዚያ በኋላ አትነቀፈም፡፡ ከታላቁ መምህር ተማር፡፡ የደግነት ቃላት ለነፍስ መድኃኒት ናቸወ፡፡ ያወቁትን የእግዚአብሔር ቃል፤ በሥራ ላይ ሲያውሉት ፈዋሽነት አለው:: የቁልምጥ ንግግር ለተናጋሪውም ለሰሚውም መርገም እንጂ በረከት አያመጣም:: GWAmh 102.1
ወንድሜ የክርስቶስን ደግነት፣ ትዕግሥትና ጨዋነት ለመግለጥ ሃላፊነት አለብህ፡፡- በጉባዔ ፊት ስትናገር አነጋገርህ የክርስቶስ አገልጋይነት ይመስክር፡፡ «ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽህት ናት፣ በኋላም ታራቂ፣ እሽ ባይ፣ ምህረትና በጐ ፍሬ የሞላበት፣ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት፡፡› (ያፅ. 3፡17) ተግተህ ጸልይ፡፡ ከራስህ የሚወጣውን ክፋት ጨቁነህ ያዝ፡፡ በአንተ ላይ ባለው በእግዚአብሔር ጸጋ ጠባይህን ልታርም ትችላለህ፡፡ ተከታዮችህ አንተ አንዳስብኸው ሳይሠሩ ሲቀሩ በቁጣ አትደንፋባቸው፡፡ ጌታ በቁጡ አነጋገርህ ተቀይሞብሃል፡፡ GWAmh 102.2
ፈቃድህን ለእግዚአብሔር ፈቃድ አስገዛ የጌታችን የየሱስ ክርስቶስ ዕርዳታ ያስፈልግሃል፡፡ ከከናፍርህ የሚወጡት ቃላት ንጹሃንና የተቀደሱ ይሁኑ፡፡ ወንጌላዊ ስለሆንህ ተከታዮችህ ብዙዎች ናቸው፡፡ በማንኛወም ጊዜ ልጆችን በደግነት ዓይን መመልክት አለብህ፡፡ GWAmh 102.3
ሥራህን በራስህ ኃይል ብቻ ለማካሄድ ካልወሰንህ እግዚአብሔር የፈለገብህን ደረጃ ልትደርስ ትችላለህ፡፡ ክርስቶስን በሥራም በቃልም ለመምሰል ስትጥር ተጨማሪ ኃይል ይሰጥህአል። በጥረትህ የእግዚአብሔር መልአክት አንዲረዱህ የዋህና ትሁት መሆን የራስህ መብት ነው፡፡ ክርስቶስ የሞተው ያንተና የተከታዮቹ ሕይወት በሙሉ የእርሱን እንዲመስል ነው፡፡ በመድኃኒትህ ኃይል የክርስቶስን ጠባይ ልታሳይ ትችላለህ፡፡ የተጣመመውን ለማቃናት፣የሻከረውን ለማለስለስ የምትችል ከዚያ በኋላ ነው፡፡ GWAmh 102.4