የወንጌል አገልጋዮች
የኢሣይያስ ቁምነገረኛነት
እግዚአብሔር ኢሣይያሰን ሳይልከው በፊት የመቅደሱን ቅዱስ ተቅዱሳን በራዕይ አሳየው፡፡ በራዕዩ መጋረጃዎቹ ተገልጠው ሁሉንም በግልጽ ተመለከተ፡፡ በተጨማሪም እግዚአብሔር በታላቅ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ክብሩ ቤተ-መቅደሱን ሞልቶት ታየው፡፡ በዙፋኑ ዙሪያ የሚያበሩ ሱራፌል ቆመው: ያማረ መዝሙራቸውን ሲዘምሩ የመሬት መናወጥ እንደተሰማው ሁሉ የመቅደሱ ምሶሶ ተነቃነቀ፡፡ ኃጢዓት ባላረከሰው ከንፈራቸው የሚዘምሩት መዝሙር እንዲህ ይል ነበር፡፡ «ትዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ:: ምድር ሁሉ በክብሩ ተሞልታለች» GWAmh 13.1
ሱራፌል አምላክን ከማክበራቸው የተነሳ ለአንድ አፍታ እንኳ ቢሆን አምላክን ከማሞገሥ አልፈው ስለራሳቸው ማማር ኩራት አይሰማቸውም፡፡ ለወደፊቱ ምድር በሙሉ በእግዚአብሔር ክብር ስትሞላ «ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” የሚለው መዝሙር ከጽንፍ እስከ አጽናፍ ሲያስተጋባ ድምቀቱ ተሰማቸው፡፡ ከእግዚአብሔር አጠገብ ሆነው እርሱን ሲያመሰግኑ መኖር ሙሉ የልብ ደስታ ስለሰጣቸው ሌላ ምንም አይመኙም፡፡ GWAmh 13.2
ነቢዩ ይህን ሁሉ ሲያዳምጥ የእግዚአብሔር ኃይል፣ ክብር፣ግርማ ተገለጠለት፡፡ በተጨማሪም በዚህ አንፃር የራሱ ጉድለት ግልጽ ብሎ ታየው፡፡ አነጋገሩ ሳይቀር የረከሰ መስሎ ተሰማው፡፡ በትህትና «ወዮልኝ ጠፍቻለሁና ከንፈሮቼ የረከሱ ሰው ነኝ . . . ዓይኖቼ የሠራዊት ጌታ ንጉሥን አይተዋልና» የኢሣይያስ ትህትና ከልብ ነበር፡፡ መለኮትና ሰው በፊቱ በራዕይ አማካይነት ሲነፃፀር ራሱን ከምናምን ቀጠረው:: የእግዚአብሔር ፍላጐት ለህዝቡ እንዴት ይገለጥላቸው፡፡ «ከሱራፌልም አንዱ ወደእኔ አየበረረ መጣ በአጁም በጉጠት ከመሰዊያው የወሰደጦ. ባና:ም ነበር: አፌንም ዳሰሰበትፍ- አነሆ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል በደልህ ከአንተ ተወገደ ኃጢዓትህ ተሰረየልህ አለኝ፡፡› ኢሣያይስ 60:1-8 ተመልከት፡፡ GWAmh 13.3
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር «ማንን ልላክ ማንስ ይሄድልኛል» ሲል ኢሣይያስ ሰማ፡፡ ኢሣይያስም በመለኮት ድጋፍ ታምኖ «እኔን ላከኝ አልሁ” ሲል መለሰ፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የእግዚአብሔር ፍጽምና በግልጽ ሲታያቸው የራሳቸው ጉድለት ይከሰታቸዋል። ምናልባት ጉድለታቸውን ሲያዩ ተስፋ ይቆርጡ ይሆናል፡፡ ‹ጠፍቻለሁ» ለማለት ይቃጣቸው ይሆናል፡፡ ግን ኢሣይያስ አንዳደረገው ትሁታን ከሆኑ ለነቢዩ የተፈጸመው ይፈጸምላቸዋል፡፡ አፋቸው በፍም ሲነካ የራሳቸውን ጉድለት እረስተው የአምላካቸው ታላቅነት ይታወሳቸዋል፡፡ ብርታት እንደሚሰጣቸውም ይሰማቸዋል፡፡ የተላኩበትን ሥራ ታላቅነት ተመልክተው ከማዕረጋቸው የሚያዋርዳቸውን መጥፎ ልምድ ሁሉ ጣል እርግፍ ያደርጉታል፡፡ GWAmh 13.4
ፍሙ የፍጽምና ምልክት ነው:: በተጨማሪም የእግዚአብሔርን ዕውነተኛ አገልጋዮች ጥረት ያመለክታል፡፡ ከንፈራቸው በአምላክ እስከሚነካ ድረስ ቅዱሳን ለሆኑት ወደመከሩ ሂዱ እረዳችሁአለሁ የሚል ተስፋ ተሰጥቶአቸዋል፡፡ እንደዚህ ሆኖ የተዘጋጀ አገልጋይ ለዓለም ጠቃሚ ነወ:: የሚነገራቸው ቃላት ዕውነትን ንጽህና የፍቅር ለዛ: ተግባሩም ቅንና ለደካሞች በረከት: ሥራውን፣ ሀሳቡን፣ቃሉን የሚቆጣጠረው የማይለየው ክርስቶስ: ኩራትን፣ ምኛትን፣ ራስን መውደድን ለማሸነፍ ታጥቆ ተነስቷል፡፡ ይህን ለመፈጸም ሲጣጣር መንፈሣዊ ብርታት ያገኛል፡፡ በየቀኑ ከአምላክ ጋር በመገናኘት የእግዚአብሔር ቃል ዕውቀቱን ያዳብራል፡፡ ግንኙነቱ ከአብና ከወልድ ጋር ስለሚሆን በእየዕለቱ የመለኮትን ፈቃድ ያሟላል፡፡ ይህን አንደፈጸመ መጠን የተጉላሉ ነፍሳትን ወደ አምላክ ለመመለስ የሚስተዋል ንግግር ለመናገር GWAmh 14.1