የወንጌል አገልጋዮች
የሥራው ቅዱስነት፡፡
ወንጌላዊ ለሕዝብ የአምላክ አፈ-ንጉሥ ነው፡፡ በሀሳብ በነገርና በተግባር የእግዚአብሔር ወኪል ሊሆን ይገባዋል፡፡ ሙሴ የኪዳን መልዕክትኛ ሆኖና ሲመረጥ የተሰጠው ትዕዛዝ «አንተም በእግዚአብሔር ፊት ለሕዝብ ሁን» የሚል ዛሬም ቢሆን ሙሴን የመረጠ አምላክ ሰዎችን ይመርጣል፡፡ ግን ቅዱሱን ጥሪ ላቀለለ GWAmh 12.4
በናዳብ በአቢሁም ላይ የደረሰው ቅጣት እግዚአብሔር ሥራውን የሚያቃልሉትን ሰዎች እንዴት እንደሚቆጣጠራቸው ግልጽ ማስረጃ ነው:: የተጠቀሱት ሰዎች ለክህነት ተመርጠው ነገር ግን ኃላፊነታቸውን አክብረው ራሳቸውን አልተቆጣጠሩም፡፡ ራስን ያለመግዛት ልምድ ተብትቦ አሥሮአቸው ነበር፡፡ ሕዝቡ አምላኩን ሲያመሰግን መስዋዕቱን ባልተለመደ አሳት ለኩሰው ስካር ተጫጭኖአቸው ይህን ፈጸሙ እንጂ ለሁል ጊዜው መስዋዕቱ የሚቃጠለው አምላክ ከሰማይ ባወረደው አሣት ነበር:: ለዚህ ጥፋታቸው ቅጣት እሳት ከሰማይ ወርዶ አመድ አደረጋቸው:: ኢሣያሰ 52: 7፤9፤1ዐ፣ 18:19 ዘሌዋዊያን 10:1-7:: GWAmh 12.5