የወንጌል አገልጋዮች
አርሳው ይህ ዓለም ነው፡፡
«በገሊላ መካከል ሲመላለስም ሁለት ወንድማማቾች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስንም መረባቸውንም ወደባሕር ሲጥሉ አየ፡፡ አሣ አጥማጆች ነበሩፍ እርሱም በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው፡፡ ወዲያው መረባቸውን ትተው ተክተሉት፡፡ ከዚያም ብሎ ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቅዋብና ዮሐንስ ከአባታቸው ጋር መረባቸውን ሲያበጁ ጠራቸውም፡፡ እነርሱም ወዲያው ታንኳቸውንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት፡፡” GWAmh 14.2
እነዚህ ሰዎች ምንም የደሞዝ ተስፋ ሳይሰጣቸው ያለማወላወልና ያለጥያቄ መክተላቸው የሚያስደንቅ ነው፡፡ ግን የክርስቶስ የጥሪ ቃል ኃይል ነበረበት:: ክርስቶስ እነኚህን ሰዎች በሠይጣን ወጥመድ የተያዙትን ሰዎች ነፃ ለማውጣት መሣሪያ አድርጐ ሊጠቀምባቸው ነው፡፡ ይህንን ሲያከናውኑ ከወግና ከልማድ ጋር ያልተቀላቀለውን የክርስቶስን ዕውነት በማዳረስ ምስክሮች መሆናቸው ነው፡፡ ክአርሱ ጋር በመኖርና በመሥራት ሰው አጥማጆች ሊሆኑ ነው፡፡ GWAmh 14.3
የመጀመሪያዎች የወንጌል አገልጋዮች የተመረጡት በዚህ መልክ ነበር፡፡ ለሶስቱ ዓመታት ከእርሱ ጋር ሠሩ:: በፈዋሽነቱ በመምህርነቱ፣ አራአያነት ለሥራው ተዘጋጁ:: ደቀመዛሙርቱ በሃይማኖት፣ በንጹህና በትሁት አገልግሎት አማካይነት ለእግዚአብሔር ሥራ ያለባቸውን ኃላፊነት ተገነዘቡ:: ከሐዋርያት የሕይወት ታሪክ የምንማረው ታላቅ ትምህርት አለ፡፡ እነዚህ ሰዎች በዕምነታቸው አንደ ብረት ነበሩ፡፡ የማይደነግጡና የማይፈሩ ሰዎች ነበሩ፡፡ ማቴዎስ 4:18-22:: GWAmh 15.1
እግዚአብሔርን የሚያከብሩና በትጋት የሚታዘዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ ከፍተኛ ዓላማና ታላቅ ሀሳብ ነበራቸው፡፡ በተፈጥሮ አንደማንኛውም የእግዚአብሔር ስራተኛ ደካሞች ነበሩ፡፡ ግን በእግዚአብሔር ላይ ሁሉ ዕምነት ነበራቸው፡፡ ሀብታቸው የአዕምሮ ሰላምና የልብ ደስታ፡: ይህ ሀብት እግዚአብሔርን መጀመሪያና መጨረሻ የሁሉም የበላይ አድርጐ ለሚቀበል ሁሉ የሚሰጥ ነው:: በክርስቶስ መምህርነት የሚሰጣቸውን ትምህርት ለመቀበል ብዙ ጨረሰባቸው፡፡ ቢሆንም ልፋታቸው ያለዋጋ አልቀረም፡፡ ከኃይል ሁሉ ምንጭ ጋር ተሳሰሩ፡፡ ስለዘለዓለም ዕውነት ጥልቅ፣ ከፍተኛና ሰፊ ማስተዋል እንዲኖራቸው ሌሊትና ቀን ያለማቋረጥ ይጥሩ ነበር: የዕውነትን መዝገብ ለዓለም በግልጽ ሰማቅረብ ሙሉ ምኛታቸው ነበር፡፡ GWAmh 15.2
የእግዚአብሔርን መንግሥት ለጠማማው ዓለም ለማስተዋወቅ ቀጥ ብለው የሚሠሩ እንደነዚህ ያሉ ቅን ሰዎች ዛሬም ያስፈልጋሉ፡፡ ዓለም አጥልቀው የሚያስቡ፤ መመሪያ ያላቸው፣ በእየቀኑ በዕውነተኛ ዕውቀት የሚጎለምሱ ሰዎች ያስፈልጋታል፡፡ ለሕዝብና ለነገድ ለቋንቋም ሁሉ ወንጌል ይዳረስ ዘንድ የስኑጽሑፍን መሣሪያነት ከፍ ባለ ጥበብ ሊጠቀሙበት የሚችሉ ሰዎች ያስፈልጋሉ፡፡ GWAmh 15.3