የወንጌል አገልጋዮች

59/217

ዕውነተኛነተ

ዕውነተኛነት በጣም ይፈለጋል፡፡ ጊዜው ስለተገባደደ ክርስቶስ አንደሠራ ለመሥራት ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ያስፈልጋሉ፡፡ በጸጥታ አየጸለዩ መኖር ብቻ አይበቃም፡፡ ተማጽኖ ብቻ የዓለምን ቸግር አያቃልልም፡፡ ሃይማኖት ካልሠራንበት ሕይወታችንን አይገዛውም፡፡ በአፍ ብቻ የሚገለጥ ሀተታ አይደለም፡፡ GWAmh 88.4

ብርቱዎች፣ ዕውነተኞች፣ ለሌሎች ዕውነትን ለማካፈል የምንጓጓ ንቁ ክርስቲያናት መሆን አለብን፡፡ ሰዎች የወንጌልን የምሥራች መስማት ያጓጓቸዋል፡፡ ሊደርሳቸው የሚችለውም በዕምነት ላይ በተመሠረተ ዕውነተኛ ሥራ አማካይነት ነው። ለሰዎች ሊጸልይላቸው፣፤ ሊሠራላቸውና ሊፈለጉ : ዕውነተኛ ተማጽኖና ልባዊ ጸሎት መቅረብ ይገባዋል፡፡ የተለምዶ ጸሎታችን ከልብ በመነጨ ዕውነተኛ ጥያቄ መተካት አለበት፡፡ GWAmh 88.5