የወንጌል አገልጋዮች
ትህትና
የእግዚአብሔር አገልጋይ ጥልቅ ትህትና ሊኖረው ይገባል፡፡ በእግዚአብሔር ሥራ ላይ ብዙ ልምድ ያላቸው ሰዎች ራስን ከማስታበይና ከኩራት የራቁ ናቸው፡፡ ክርስቶስን ስለሚያከብሩት የሚክበሩ ራሳቸውን ዝቅ ሲያደርጉ መሆኑን ያውቃሉ፡፡ GWAmh 87.4
ሙሴ ከሲና ተራራ ሲወርድ ፊቱ ማንጸባረቁን አልተገነዘበም ነበር፡፡ ጳውሉስም ስለወንጌል አገልግሉት አርምጃው በጣም የትህትና አስተሳሰብ ነበረው፡፡ ስለራሱ ሲናገር ከኃጢዓተኞች ሁሉ የባሰ ኃጥዕ መሆኑን ገልዷል፡፡ «አሁን እንዳገኘሁ አይደለም፣ ነገር ግን ስለእርሱ በክርስቶስ የሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብየ» ቢሆንም ጳውሎስ በእግዚአብሔር የከበረ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ GWAmh 87.5
መድኃኒታችን፣ ዮሐንስ መጥምቁ ከነቢያት ሁሉ የበለጠ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ግን ዮሐንስ ስለራሱ ሲጠየቅ የክርስቶስን የጫማ ክር ሊፈታ አንኳ የማይገባው ዝቅተኛ ሰው መሆኑን ተናገረ:: ደቀመዛሙርቱ ሰዎች ሁሉ ክርስቶስን ይከተላሉ ብለው በማጉረምረም በነገሩት ጊዜ የክርስቶስ መንገድ ጠራጊ መሆኑን ገለጠላቸው፡፡ GWAmh 88.1
የዚህ ዓይነት መንፈስ ያላቸው ሰዎች ዛሬም ይፈለጋሉ፡፡ ራሳቸውን ብቁ አድርገው የሚገምቱ ሠራተኞች ለክርስቶስ ሥራ አይጠቅሙም:: GWAmh 88.2
አምላካችን ለሥራው የሚፈልጋቸው በክርስቶስ ደም ለመንጻት የሚፈልጉትን፣ በራስ ትምክህት ሳይሆን በጌታ አምነው ሥራውን የሚጀምሩትን፤ ከሰዎች ጋር ለመግባባት የክርስቶስ ዕርዳታ የሚገነዘቡትን ሰዎች ነው: GWAmh 88.3