የወንጌል አገልጋዮች
ሙሉነት
ብዙዎች ክርስቲያን ነን ባዮች ፍጹማን ያልሆኑና አዙረው የማይመለከቱ ናቸው፡፡ ሊማሩት የሚገባቸውን ትምህርት በጥራዝ- ነጠቅነት መማራቸው ያስታውቅባቸዋል፡፡ በትህትና ክርስቶስን ለመምሰል የሚሞክሩ አፋዊ ትህትናቸውን በሥራ አያሳዩም:: አንዳንዶች ደግሞ ትጉዎችና ታታሪዎች ቢሆኑም ኩሩዎች ናቸው፡፡ ትህትና ሲያልፍም አይነካካቸውም፡፡ ደግሞ ሌሎች በሥራቸው ውስጥ ክርስቶስን አያስታውሱም፡፡ መልካም ጠባይ ያላቸውና አዛኞች ቢሆኑም ስለመድኃኒታችን ያላቸው ዕውቀት ስለሰማይ ምንም የማያውቁ መሆናቸውን ያጋልጣቸዋል፡፡ ክርስቶስ ይጸልይ አንደነበር አይጸልዩም፤ ለነፍሳት የከበረ ግምት አይሰጡም፤ በሥራቸው ከችግር ጋር መታገልን አልተማሩም፡፡ ሌሎች ደግሞ የመለወጥ ኃይል ያለውን ክርስቶስን በመዘንጋት ተችዎች፣ ሐሜተኞችና እቡዮች ይሆናሉ፡፡ አንዳንዶችም የማይጸነና ከጊዜው ጋር የሚዘሙ ወላዋዮች ናቸው:: ምንም ያህል ቃለ-እግዚአብሔር በሰፊው ቢነገር የተነገረው ቃል በዕለት ኑሮ ካልሠራ የመመለስ ኃይሉ የተወስነ ይሆናል፡፡ GWAmh 88.6
ያልተስተካክለ ሥራ የሥራተኛውን ልብ ያደነድናል፤ አእአምሮውንም ያደነዝዛል፣ ለሌሎችም እንቀፋት ይሆናል፡፡ GWAmh 89.1