የወንጌል አገልጋዮች
ከክርስቶስ ጋር አንድነት
ከዋናው ጠባቂ ከክርስቶስ ጋር የተባበረ ዝቅተኛ ጠባቂ ክርስቶስን በቀላሉ ለሰዎች ሊያስተዋውቅ ይችላል፡፡ የዕምነታችን መሠረተ-ትምህርትን ጠንቅቆ ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ GWAmh 87.1
ከዚህ የበለጠ ጠቃሚ ነገር ወንጌላዊው በሚያስተምረው ትምህርቱ ራሱ የተጠቀመብት እንዲሆን ነው:: ከክርስቶስ ጋር አንድነት ያለው ወንጌላዊ ለእግዚአብሔር ማገልገል የበለጠ ምኞትና ችሎታ ይኖረዋል፡፡ ዕውቀቱ ይጠልቃል፡፡ ምክንያቱም በፀጋ ማደግ ማለት ቃለ-እግዚአብሔርን በበለጠ ማስተዋል ማለት ነው፡፡ በጌታው እጅ ያለ መሣሪያ መሆኑን ያምንበታል፡፡ ካልተፈተነ በቀር ጉድለቱን ሊያውቅ ስለማይችል ፈተና ይደቀንበታል፡፡ ቢሆንም ጌታን በፍጹም ልቡ ከተማጸነ ፈተናው ሁሉ ያልፋል፡፡ GWAmh 87.2
አንዳንድ ጊዜ ይወድቅ ይሆናል፡፡ ውድቀቱ ግን ምክንያትና በጌታው ላይ የበለጠ እምነት አንዲኖረው መገፋፊያ ይሆናል፡፡ ቢሳሳትም ስህተቱን ላለመድገም ይጥራል፡፡ ፈተናን ለመቋቋም የበሰጠ ብርታት ይኖረዋል፣ ሌሎችም በአራአያነቱ ይጠቀማሉ፡፡ GWAmh 87.3