የወንጌል አገልጋዮች
የወንጌላዊያን አራአያነት
ክርስቲያናት ወንጌላዊያን ከሥራቸው ጋር የሚስማማ አራአያነት ለወጣቶች ማሳየት አለባቸው፡፡ ወጣቶች ግልጽና የሚሠሩት ሥራ ሁሉ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ይርዱአቸው:: በየቀኑ ፍሬ የሚያፈራ ዘር መዝራት አለባቸው፡፡ ጉድለታቸውንና እንከናቸውን አስወግደው ሁል ጊዜ የመምህርነት ኃላፊነት ሊሰማቸው ይገባል፡፡ GWAmh 77.5
የሚፈለገው የመንፈስ ጽናትና የልብ ንጽህና ነው፡፡ ንጹህ ግብረ-ገብ የትክክለኛ አስተሳሰብና የቅን ሥራ ውጤት ነው፡፡ ክፉ ሀሳብ ሕይወትን ሲያበላሸ የተገታ አስተሳሰብ ከጌታ ጋር ተባባሪ ሠራተኛ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ማንኛውም አስተሳሰብ በክርስቶስ ሥር መገዛት አለበት፡፡ GWAmh 78.1
የወንጌል ገበሬዎች በሥራቸውና በንግግራቸው የተጠነቀቁ ጠቢባን መሆን አለባቸው፡፡ መንጋዎችን በተፈለገው የሚመግቡ፣ የኑሮንና የሕይወትን ዝቅተኛ ደረጃ በምንም መንገድ የማይደግፉ፣ ሃይማኖትን የሚያጠነክርና ነፍስን አንጽቶ ሥጋዊን ሀሳብ የሚያስወግድ ፍቅር ያደረባቸው ሰዎች መሆን አለባቸው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሠራተኞች ምድራዊነት አያጠቃቸውም፡፡ ፈተና በቀላሉ አይገረስሳቸውም (አይጥላቸውም)፡፡ ሰውነታቸውን ያበረታሉ፡፡ ፊታቸውን ወደ ጽድቅ ሙራ ይመልሳሉ፡፡ GWAmh 78.2
በመጽሐፍ ቅዱስ መሪነት የሚራመድ ሰው ግብረ-ገብነቱ አይደክምበትም፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መሪነትና አነቃቂነት አዝማሚያ ያለ አስተሳሰቡ ሁሉ ንጹህ ይሆናል::- ከክርስቶስ ከፍቅር በቀር ስሜቱን የሚስበው፣ አረማመዱን የሚመራው፤ ንቃትና ጽናት የሚሰጠው ምንም ሌላ ነገር የለም፡፡ ፍቅሩ በዕድገት መስመር ይመራዋል፡፡ ተፈላጊ ሀሳብ ያፈልቅለታል፡፡ ራስን የመግዛት ትምህርት ያስተምረዋል፡፡ የሚሠራውን ሥራ ሁሉ ክቡር ያደርግለታል፡፡ GWAmh 78.3
ወጣቱ አጉል ጠባዩን አንደ ጨርቅ አውልቆ ጥሎ አዲስ የጠባይ ፀጋ ሊለብስ የሚችለው በምን አማካይኝነት ነው? GWAmh 78.4
«እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ፣ ወይም ማናቸውንም ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት::” ሀሳብን፣ ፍላጐትንና ሥራን የሚገታ መምሪያ ይህ ነው፡፡ ርኩስ ፍላጐት መወገድ አለበት፡፡ በክፉ ፍላጐት ፈንታ ቅዱስ ፍላጐትና መልካም ምኞት የልብን መቀደስ ሊያይዝ ይገባል፡፡ የሕሊና ዳኝነት ችላ ሲባል የሕይወት እርምጃ ወደ ታች ያዘቀዝቃል፡፡ ጳውሎስ «በክርስቶስ በሚያስችለኝ ሁሉን አደርጋለሁ» ይላል GWAmh 78.5
ወደ የሱስ ብትቀርብና ሥራህን በክርስቶስ ሥር ብታስገዛው አግሮችህ ከትክክለኛው መንገድ ዝንፍ አይሉም፡፡ በጸሎት ብትተጋ፤ ሁልጊዜም በክርስቶስ ፊት አንዳለህ ቢሰማህ፤ ያለ ኃጢዓትና ያለነውር ልትሆን ትችላለህ፡፡ ዕምነትህ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የጸና ከሆነ በእግዚአብሔር መንግሥት የድል አክሊል ተትቀዳጃለህ፡፡ የመንፈስ ፍሬዎች ፍቅር፣ ደስታ፣ ትዕግሥት፣ ጨዋነት፣ መልካምነት፣ ዕምነት፣ ትህትና፣ መሻትን መግዛት፣ ናቸው፡፡ እንዲህ ባሉት ላይ ሕግ የለባቸውም፡፡ ክርስቶስ በውስጣችን ካለ ሥጋችን እስከነፍትወቱ አንሰቅለዋለን፡፡ GWAmh 79.1