የወንጌል አገልጋዮች
የአክብሮት ፀጋ
ለክርስቶስ የሚሠሩ ሰዎች ቅኖች፤ ታማኞች፣ ለሚያምኑበት ነገር አንደቋጥኝ የጸኑ፣ በዚያውም ላይ አክባሪዎች መሆን አለባቸው፡፡ አክብሮት ከፀጋ በረከቶች አንዱ ነው፡፡ ከሰዎች ጋር ተስማምቶ መኖር ካስቸጋሪዎቹ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ይህን ችግር ለማለፍ የሚችል ሰው «ሩህሩሆችና ትሁቶች ሁኑ» (1ኛሌኤጥ. 3፡8) የሚለውን መመሪያ ጠንቅቆ ያስተዋለ ብቻ ነው፡፡ በክርክር ሊቃና ያልቻለው፣ በፍቅር አማካይነት ይሳካል፤ ኩርፊያ ያልታሰበች መልስ፣ ከልብ ያልሆነ ትህትና ወዳጅነትን አጥፍቶ አለመግባባትን ይተካል፡፡ GWAmh 74.3
ክርስቲያን ክርስቶስ በዚህ ምድር የኖረውን ኑሮ ዓይነት ለመኖር መሞከር አለበት፡፡ ምሣሌነቱ በንጹህ፣ ኃጢዓት የለሽ ሕይወቱ ብቻ ሳይሆን በትዕግሥት፣ በጨዋነቱና ረጋ ባለ ሰውነቱ ጭምር ነው፡፡ ሕይወቱ በትህትና የተመራ ላዘኑትና ልባቸው ለተሰበረው አጽናኝና ደግ የእርሱ መገኘት ለቤተሰቦች ደስታ ነበር፡፡ ሕይወቱ በማህበራዊ ኑር ውስጥ እንደ አርሾ ይሠራ ነበር፡፡ GWAmh 74.4
በጠማማ ቀራሙች ፊት፣ ባልነጹት ሳምራዊያን መካከል፤ በአሕዛብ ወታደሮች ፊት፣ ባልተማሩት ተራ ሕዝብ መካከል፣ በውጥንቅጥ ሕዝብ መካከል ያለ ነውር ኖረ፡፡ ለሁሉም የርህራሄ ቃላት ይናገራቸው ነበር፡፡ የደከሙና ሸክም የከበደባቸው ሰዎችን ባጋጠመው ቁጥር የሸክማቸው ተካፋይ ከመሆኑም በላይ ከሕይወት ቃል ያሰማቸው ነበር፡፡ ተስፋ የቆረጡትንና ግዴለሾችን አስተምሮ የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን ተስፋ አንዲያድርባቸው ለማድረግ ይጥር ነበር፡፡ የክርስቶስ መምህርነትና ሕይወት ሸካራውን ያለሰልሳል፣ ወጀቡን ያስተካክላል፡፡ ቃላቱ ጨዋነትን ያዘሉ፤ አነጋገሩ ማራኪ ነበር፡፡ ንጽህናንና መግባባትን ማዋሃድ ከክርስቶስ እንማር፡፡ ክርስትናን በበለጠ ሊመሰክርና ሊያስተዋውቅ የሚችል ትሁትና ደግ ክርስቲያን ብቻ ነው፡፡ GWAmh 75.1
መልካም ቃላት ለነፍስ እንደጠል ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ክርስቶስ «የደከመውን በቃል እንዴት እንደሚደግፍ ያውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶታል፡» (ኢሳ 50:4) ተብሏል፡፡ እኛም «ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ በጨው እንደተቀመመ በፀጋ ይሁን፡፡” ተብለናል፡፡ ከአንተ ጋር ያሉት ትህትና ቢጐድላቸው አንተ ትህትናህን አታጉድል፡፡ መከበርን የሚወድ የሌሎችን ክብር መንካት የሰበተም፡፡ ይህን ሕግ የተማረ ያልተማረ ሳይባል ሁሉም ማክበር አለበት፡፡ እግዚአብሐር በዝምተኞች ሰዎች የሚፈጽመው ስለማይታወቅ እነርሱም መከበር አለባቸው አልባሌ ሰዎችን ለሥራው ታላቅ ሰዎች አድርጐአቸው ባለፈው ጊዜ ታይተዋል፡፡ መንፈሱ የሰዎችን ስሜት ያነቃቃል፡፡ GWAmh 75.2
ጌታ ያልተጠረቡትን ደንጊያዎች የከበሩ አድርጐ ከታላቅ ሙያ ላይ አውሉአቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ሰው እንደሚያይ አይመለከትም፡፡ ልብ አይቶ በጽድቅና በእውነት ይፈርዳል አንጂ የፊት-ገጽ ተመልክቶ አይፈርድም፡፡ GWAmh 75.3
ጌታ የሱስ የማንንም መብት እንዳንነካ በጥብቅ ያስጠነቅቀናል፡፡ የሰዎች ማህበራዊና ክርስትና መብቶች መዘንጋት የለባቸውም፡፡ ሰዎች ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ልጆች መቆጠር አለባቸው። ክርስትና ሰውን ጨዋ ያደርገዋል፡፡ ክርስቶስ ለሚያሳድዱት ሳይቀር ትሁት ስለነበር ተከታዮቹ የእርሱን አራአያነት መከተል አለባቸው፡፡ ጳውሎስ በገዥዎች ፊት ሲቀርብ እንዴት ነበር? በአግሪጳ ፊት ቀርቦ ሲናገር መልካምና የተማረ ሰው፤ ንግግሩ በትህትና የታጀበ ነበር፡፡ ወንጌል የሚያዘው ለይስሙላ (ለይምሰል) የሚታየውን ትህትና ሳይሆን ከልብ የመነጨ ትህትና ነው፡፡ GWAmh 75.4
የተጣመመን ፍርድና መርዘኛን ንግግር ለመክደን የሚደረገው ውጫዊ ትህትና በክርስቶስ ዘንድ የተከሰሰና የተናቀ ነው፡፡ የእውነት ትህትና ከሰውየው ሕይወት ጋር የተዋሃደ ነወ:: ፍቅር በልቡ ውስጥ ማደር አለበት:: እውነተኛ ክርስቲያን ለጌታው የሚያበረክተው አገልግሉት ከልቡ የመነጨ ነው:: ስለ ክርስቶስ ባለው ፍቅር አማካኝት ባልንጀራውን እንደ ራሱ : ፍቅር የደግነትን ጨረር ይፈነጥቃል፡፡ GWAmh 76.1
ፊትን ያበራል፤ ድምጽን ያለሰልሳል፡፡ የክርስቲያኑን ሕይወት ከፍ ያደርጋል፡፡ ለዚህ ቅዱስ አገልግሎት ለተሰለፉ ሰዎች «እናንተ የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ ሰዎች ሆይ ርኩስን አትንኩ» (ኢሣይያስ 52:11) የሚል ማስጠንተቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ለእግዚአብሔር ልዩ ሥራ ለመሥራት ክብርና ሞገሥ ያገኙ ሰዎች የሚናገሩት ቃል ከሚፈጽሙት ተግባር ጋር መስማማት አለበት፡፡ በትሁት ቃላቸው የሰዎችን ሕይወት ሊያሻሽሱ የሚችለ-፤ በፈተና ሕይወታቸው የማይናጋ፣፤ ሀሳባቸው ዋናው ዓላማቸው ነፍሳትን ለማዳን የሆኑ መሆን አለባቸው::: GWAmh 76.2
በወንጌል ሥራ ላይ ሰይጣን የተለየ የፈተና ወጥመድ ያጠምዳል፡፡ ወንጌላዊያን መለኮታዊ ዕርዳታ ካልጨመረላቸው በቀር ፈተናውን ለመቋቋም የማይችሉ ሰብዓዊ የወንጌል ባላደራዎች መሆናቸውን ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ወንጌላዊያን በእግዚአብሔር የተመረጡ ሕይወታቸውን ለዘለዓለማዊ አምላክ ቢያስገዙ ታላቅ ሞያ ሊፈጽሙ የሚችሱ ሰዎች መሆናቸውን ሰይጣን ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ኃጢዓት ቢሠሩ በሕይወታቸው ውስጥ ኃጢአት ጐልቶ መታየቱን በማወቅና የክፉ አገልጋዮች ሊሆኑ አንደሚችሉ በመገንዘብ ባለው ጉልበቱና፣ ብርታቱና ዘዴውም የኃጢያት ባሪያዎች ሲያደርጋቸው ይጥራል፡፡ GWAmh 76.3
ለወንጌል ሥራ የተጠሩ ሰዎች ለሥራው ገጣሚ መሆናቸውን ማስመስከር አለባቸው፡፡ ክርስቶስ «በስራችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ» (በ፲ኛ ጴጥሮስ 1:15) ሲል አዝዛል፡፡ ጳውሎስም «ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ በእነዚህም ጽና:: ይህን ብታደርግ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና” (ጢሞቲዎስ 4:12:16) ሲል ጽፏል! ጴጥሮስም «ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ : እንግዲህ አንደባለ አእምሮ (፲፪ኛ ጴጥሮስ 4:7) ይላል፡፡ ንጽህናና ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡ የዚህ የተበላሽ ዓለም አመዓ አንዳይበክለን መጠንቀቅ አለብን፡፡ የወንጌል መልዕክትኞች ባገቡም ሆነ ባላገቡ ሴቶች ዘንድ ዝናና ታዋቂነት ለማትረፍ ልዩ ጥረት አያድርጉ: ለሁሉም ትሁትና ገር ቢሆኑም ክብራቸውን መጠበቅ አለባቸው፡፡ በእንዲህ ያለ የግዴለሽነት ተግባር ኃጢዓት ይሳሳባል፡፡ GWAmh 76.4
ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በንጽህና ይኖር ዘንድ መክሮታል፡፡ ይህ ዓይነት መምክር ለዘመኑ ሰዎችም ያስፈልጋል፡፡ ለሠራተኞቻችን የንግግርና የሥራ ንጽህና ሊኖር ይገባል፡፡ GWAmh 77.1
ሴላ ሰው ሊሠራልን የማይችል ለእግዚአብሔር ልንፈጽመው የሚገባን የየግል ተግባር አለብን:: ዓለምን የማጓጓል ትግል ተደቅኖብናል፡፡ ከሰዎች ጋር ስንኖር ፌዘኞች ሳንሆን ቁም-ነገረኞች መሆን አለብን፡፡ GWAmh 77.2
ከፍተኛ ጥረት እንድናደርግ የሚያነቃቃን በአካባቢያችን የምንመለከተው በቂ ነገር የለም ወይ” በየቦታው የተፈቱ ቤተሰቦች የተሰናከሉ ግለሰቦች ይታያሉ፡፡ የሕይወት መመሪያ ተወላግዶአል፡ ግበረ-ገብ ወድቋል፡፡ ምድር ሶዶማዊነት አጥቅቷታል፡፡ የጥፋት ውኃ ያመጣውና በሰዶም ላይ የአሣት ዝናብ ያሰዘነበው ክፋትና ኃጢዓት በምድር ላይ በግልጽ ይታያል፡፡ ምድር በአሣት ወደምትነካበት ወደ መጨረሻው ዘመን ተቃርበናል፡፡ GWAmh 77.3
የእውነት መብራት የሚያበሩ ሰዎች ከክፋት መራቅ : ለሥራቸው አንቅፋት የሚሆነውን ሥራ እያስወገዱ በቅድስና ጉዳና ይጓዙ: አስተሳሰብን ዝቅ አድርጐ ጠባይን የሚያደኩርን፣ በመንገዱ የሚገኝን ፈተና ሁሉ መቋቋም የወንጌላዊው ሥራ ነው፡፡ በትጋተና በፀሎት ዕርዳታ ድካሙን ወደ ብርታት ሊለውጥ ይችላል፡፡ በክርስቶስ ሰዎች የግብረ-ገብ መሻሻል፤ የሐሳብ ጽናትና፣ የአስተሳሰብ ጥልቀት ሊኖራቸው ይችላሉ: የበቁ ክርስቲያናት ሊሆኑ ይችላሉ : GWAmh 77.4