የወንጌል አገልጋዮች
ማህበራዊ ግንኙነት
ወጣት ወንጌላዊያን ባልተገባ ከሴቶች ጋር በሚያደርጉት አቀራረብ ሥራቸው ሊበላሽባቸው ይችላል፡፡ እነዚህ ሴቶች በሚያደርጉት መጥፎ አረማመድ የሌሎችን ሕይወት አንደሚያበላሽ አይገነዘቡም፡፡ ይሉኝታን ቢያውቁ ለወንጌላዊና ለራሳቸው መልካም ነው፡፡ ወንጌላዊው በእንደዚህ ያለ ደረጃ ከተገኘ ለሌሎች ወደ ስህተት የሚመራ ምሣሌ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ጠቅላላው ኃላፊነት የወንጌላዊያን ነው፡፡ (፲ኛ ቆሮንቶስ 10:31፣ ፊሊጺስዩስ 4:13:93 በእግዚአብሔር መሪነት የማያስደስት ማህበራዊ ግንኙነትን ማረም አለባቸው፡ ክፉን ሁሉ ገለል አድርገው ወጣት ሴቶች የማያስደስት አቀራረብ ሲያሳዮአቸው በግልጽ ተገቢ አለመሆንን ማስገንዘብ አለባቸው፡፡ ከነውር ለማምለጥ ክፋትን : የሚጠሩ ግልጽ መሆን አለባቸው፡፡ ክርስቲያን የሆኑ ሴቶች ተግሣፅንና ምክርን መቀበል መቻል አለባቸው፡፡ GWAmh 79.2
ቀልድና ፌዝ የዓለማዊያን ሰዎች ተግባር ነው፡፡ ክርስቲያኖች በልባቸው ውስጥ ሰላም የሰፈነባቸውና ፊታቸው በደስታ የፈካ ቢሆንም ዋዛና ፈዛዛ ማብዛት የለባቸውም፡፡ ሲጸልዩ እውነተኛ ሰላም አግኝተው ሕይወታቸው ክፍ ባለ ደረጃ ሆኖ ለይምሰል ብቻ መኖር የለባቸውም፡፡ የአምልኮት ስሜት በግልጽ የተስተዋለው ወንጌላዊ ምድራዊ ደስታና ተድላን ችላ ይላል፡፡ በዓለም ውስጥ ካለው ፍተወተ-ሥጋ ነፃ ወጥቶ አምላካዊ ተጽአኖ ያርፍበታል፡፡ በወንጌላዊውና በአምላክ መካከል ያለው ግንኙነት ሲጠነክር ነፍሱ ወይም ኑሮው ከአምላክ ፈቃድ ሊወጣ : በፊቱ ተጨባጭ ተስፋ ስለሚታየው ያንን የታየወን ለሰዎች ለማስረዳት አይቸገርም፡፡ የሰዎችን አእምሮና ስሜት ለተቀደሰ አስተሳሰብ ያነሳሳዋል፡፡ GWAmh 79.3
ስለ ሥራው ቅዱስነትና ስለ ኃላፊነቱ ከባድነት ያልተረዱ አንዳንድ ወጣቶች ለእግዚአብሔር እንሠራለን ብለው ይሰለፋለ፡፡ ፃይማኖታቸው ግብዝ ከመሆኑም በላይ ነፍሳትን ለመመለስ ዕውነተኛ ጉጉት የላቸውም፡፡ አንደፈሳሽ ውኃ በተለምዶ ይጓዛሉ-:: በየለቱ ቃለ- እግዚአብሔርን ቢያደምጡም ጊዜአቸውን ከሴቶች ጋር በመላፋትና በከንቱ ያሳልፉታል፡፡ የሃይማኖትን መመሪያ ቢያውቁትም በልባቸው ውስጥ የሃይማኖት ዘር አልጎለበተም፡፡ GWAmh 80.1
እንደነዚህ ያሉት ሰዎች ራሳቸው ከሕይወት ፈሳሽ ውኃ ሳይጠጡ ሌሎችን ወደ ሕይወት ውኃ ምንጭ ሊመልሱ አይችሉም፡፡ GWAmh 80.2
አሁን ዘመኑ የቀልድና የመዝናናት ዘመን መሆን የለበትም፡፡ ዓለም የታሪክ ገጾች ሊታጠፉ ነው:: ከጥልቅ አስተሳሰብ ላላ ያሉ አእምሮዎች መሻሻል አለባቸው፡፡ ሐዋርያው ጴጥሮስ «ስለዚህ የልቦናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ የሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ፈጽማችሁ ተስፋ: አንደሚታዘሉ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ፡፡ ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ አንደሆነ እናንተም በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ» ( ጴጥ 1፡13-16) ብሏል፡፡ GWAmh 80.3
ዋዘኝነት ቀር ጠበቅ ያለ ግንኙነት ከአምላክ ጋር መደረግ አለበት፡፡ ዋናው ዓላማ እግዚአብሔርን መታዘዝ መሆን አለበት፡፡ አንድ ሰው ላራመደጡ የክርስትና ሕይወት ምሥጋና መጠባበቅ ወይም መቀበል የለበትም፡፡ ምክንያቱም ምሥጋና ከትህትና ይልቅ መመካትን ከንጽህና ይልቅ ጥፋትን ያሳድራል፡፡ በእውነት ለሥራው የበቁ ሰዎች ራሳቸው ከሥራው ቅዱስነት ጋር ሲያመዛዝኑት ዝቅተኝነት ይሰማቸዋል፡፡ GWAmh 80.4
ሥጋዊ ልቡን ወደ መንፈሳዊነተ ለመመለስ ጊዜው አሁን ነው፡፡ ምሥጋና የሚጓጓ፣ ጠበቂነቱን የሚዘነጋ፤ ባልረባ ውይይት ጊዜውን የሚያሳልፍ፤ ቀልድና ፌዝ የሚያበዛ ሳቅና ውካታ የሚወድ ወንጌላዊ ለሥራው ተገቢ አይደለም፡፡ የበጐች ጠባቂነት መብትና ግዴታ ሳይሰጠው አስቀድሞ ስለሥራው በደንብ መማር አለበት፡፡ ፲ኛ ጴጥሮስ 1:13-16:: GWAmh 80.5
የታማኝን ቄስ ቅን አገልግሉት የሚነቅፉ ወንጌላዊያን ለሌሎች በሚያሰሙት ቃል ራሳቸው አልተባረኩበትም፡፡ ስለዚህ በጌታ የወይን ቦታ ውስጥ ማገልገል የለባቸውም፡፡ GWAmh 80.6
የክርስቶስ አገልጋይ ጸሎትኛ፣፤ ሃይማኖተኛ፣ ፈገግታ የማይለየው መሆን አንጅ የማይመች፤ ቀልደኛና ፌዘኛ መሆን የለበትም፡፡ ቀጥተኝነትና ቁምነገረኛነት የወንጌላዊ ጠባዮች ናቸው፡፡ ለወንጌላዊው የአእምሮ ሰላም የሚያስገኝለትና ዘለዓለማዊ ደስታ የሚያተርፍለት የዕውነተኛን አምልኮ አስተዋይነቱ ነው፡፡ የዓለምን የኃጢዓት ረግረግ ወጥቶ የመለኮታዊ ተግባር ተካፋይ ሊሆን ይችላል፡፡ የሚያስተምሩትን የሚፈጽሙ ልባቸው የነፃ የአግዘ.አብሔር ሰዎች ይባላሉ፡ GWAmh 81.1