የክርስቲያን አገልግሎት

127/246

ምዕራፍ 12—የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ አገልግሎት

ሰማያዊው ጽንሰ ሐሳብ

የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ አገልግሎት ሰማያዊ እቅድ ነው፡፡ በዚህ የወንጌል የአገልግሎት ዘርፍ መሳተፍ የሚችሉ አያሌ ወንዶችን ሴቶች አሉ፡፡ ለእግዚአብሔር ብርቱ ሠራተኞች ወደ መሆን ማደግ የሚችሉ አገልጋዮች በዚv መልኩ ማፍራት ይቻላል፡፡ ይህን ዘዴ ጥቅም ላይ አውሎ የእግዚአብሔርን ቃል ለሺዎች በማቅረብ ሠራተኞች ከዓለም ሕዝቦችና ቋንቋዎች ጋር የግል ግንኙነት መፍጠር ችለዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ለቤተሰቦች መቅረቡን ተከትሎ የተቀደሱት እውነቶች የአባላቱን ህሊና የመንካት ኃይል አግኝተዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በግላቸው እንዲያነቡ፣ እንዲመረምሩና የራሳቸውን ፍርድ እንዲሰጡ የሚለመኑት ሰብዓዊ ፍጡሮች መለኮታዊውን አስተምህሮ የመቀበል ወይም የመቃወም ኃላፊነት አለባቸው፡፡ እግዚአብሔር በዚv የከበረ አገልግሎት ተካፋይ የሚሆነውን ሳይሸልም አይተወውም፡፡ በስሙ የሚደረገውን ማንኛውንም ጥረት የስኬት አክሊል እንዲደፋ ያስችለዋል፡፡--Gospel Workers, p. 192. ChSAmh 193.1

እኛ የምንሠራው ሥራ በሰማይ አምላክ ተለይቶ ተቀምጦአል፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳችንን አንግበን ዓለምን ለማስጠንቀቅ መገስገስ ይኖርብናል፡፡ ነፍሳትን በማዳኑ ረገድ የእግዚአብሔር ረዳት እጆች መሆን ይጠበቅብናል፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 150. ChSAmh 193.2