የክርስቲያን አገልግሎት

126/246

የወቅቱ መልእክት

እውነተኛዎቹ ወንጌላውያን፣ የሦስቱን መላእክት መልእክት የተቀበሉ እንዲሁም እግሮቻቸውን ከሰንበት ዞር ያደረጉ የቤተ ክርስቲያን አባላት በሙሉኢሳይያስ ምዕራፍ አርባ ስምንትን አጽንኦት ሰጥተው እንዲያነቡ አብልጬ ላስገነዝባቸው አልችልም፡፡ በዚህ ምዕራፍ የተስተዋለው በጎና ጠቃሚ ተግባር—ጌታ ሕዝቦቹ በዚህ ዘመን እንዲሠሩ የሚጠይቃቸው ሥራ ነው፡፡ መልእክቱ የት ላይ ገጣሚ መሆን እንዳለበትና ፍጻሜ ስለሚያገኝበት ጊዜ በጥርጣሬ ውስጥ አልተተውንም “ወገኖችህ የቀድሞ ፍርስራሾችን መልሰው ይሠራሉ፤ የጥንቱንም መሠረት ያቆማሉ፤ አንተም የተናዱ ቅጥሮችን አዳሽ፣ ባለ አውራ መንገዶች ጠጋኝ ትባላለv፡፡ እግዚአብሔር ዓለምን የፈጠረበት ምልክትና መታሰቢያ የሆነውን የሳምንቱን ሰባተኛ ቀን ሰንበት ኃጢአተኞች ሰዎች ቀይረውታል፡፡ በአምላካዊው ሕግ ላይ የተደረገውን ጥሰት ወደ ቀድሞው የመመለስ የተለየ ሥራ ለእግዚአብሔር ሕዝቦች ተሰጥቶአል፡፡ ወደ መጨረሻው በተቃረብን ቁጥር ሥራው ይበልጥ አስቸኳይና ፋታ የማይሰጥ እየሆነ ይመጣል፡፡ እግዚአብሔርን የሚወዱ ሁሉ ትእዛዛቱን በመጠበቅ አምላካዊውን ምልክት መያዛቸውን ያሳያሉ፡፡ ሕዝቦቹ የአምላካዊው ዱካ መኖሪያ ናቸው. . . ወንጌልን ከሕክምና አጣምሮ በያዘው እውነተኛ አገልግሎት ላይ ሰንበት—ታላቁ የእግዚአብሔር የፍጥረት ሥራ መታሰቢያ ቀን እንደመሆኑ በተለይ ይጠቀሳል፡፡ በዚህ ዕለት አምልኮ ማድረግ የወደቀውን ሰብዓዊው ሥነ ምግባር ከቀደመው አምላካዊው አምሳል ጋር የማስተሳሰር _ ሥራ መሥራት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በተለይ በዚv ወቅት ወደ ፊት ይዘውት ሊገሰግሱ የሚገባ አገልግሎት ነው፡፡ አገልግሎቱ በትክhል ሥራ ላይ ሲውል ለቤተ hርስቲያን በሳል በከረቶችን ያስገኛል፡፡Testimonies, vol. 6, pp. 265, ..266. ChSAmh 192.1